Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ነገሥት 10:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ሰሎሞን ከኪራም መርከቦች ጋር በውቅያኖስ ላይ የሚጓዙ ሌሎች የተርሴስ መርከቦችም ነበሩት፤ እነርሱም በየሦስት ዓመት ወርቅን፥ ብርን፥ የዝሆን ጥርስን፥ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ንጉሡ ከኪራም መርከቦች ጋራ ዐብረው በባሕር ላይ የሚጓዙ የተርሴስ የንግድ መርከቦች ነበሩት። እነዚህም በየሦስት ዓመቱ አንድ ጊዜ ወርቅ፣ ብርና የዝሆን ጥርስ፣ ጦጣዎችና ዝንጀሮዎች ያመጡ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ሰሎሞን ከኪራም መርከቦች ጋር በውቅያኖስ ላይ የሚጓዙ ሌሎች የተርሴስ መርከቦችም ነበሩት፤ እነርሱም በየሦስት ዓመት ወርቅን፥ ብርን፥ የዝሆን ጥርስን፥ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ለን​ጉ​ሡም ከኪ​ራም መር​ከ​ቦች ጋር በባ​ሕር ውስጥ የተ​ር​ሴስ መር​ከ​ቦች ነበ​ሩት፤ በየ​ሦ​ስት ዓመ​ትም አንድ መር​ከብ ከተ​ር​ሴስ ወር​ቅና ብር፥ የተ​ቀ​ረ​ጸና የተ​ደ​ረ​ደረ ዕንቍ ይዞ ይመጣ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ለንጉሡም ከኪራም መርከቦች ጋር የተርሴስ መርከቦች ነበሩት፤ በሦስት በሦስት ዓመትም አንድ ጊዜ የተርሴስ መርከቦች ወርቅና ብር፥ የዝሆንም ጥርስ፥ ዝንጀሮና ዝንጕርጕር ወፍ ይዘው ይመጡ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 10:22
21 Referencias Cruzadas  

ንጉሥ ኢዮሣፍጥ ውቅያኖስን አቋርጠው ከኦፊር ወርቅ የሚያመጡለትን የተርሴስ ዐይነት መርከቦች አሠርቶ ነበር፤ ነገር ግን መርከቦቹ በኤጽዮንጋብር ወደብ ላይ ስለ ተሰበሩ መጓዝ አልቻሉም።


የተርሴስ ደሴቶች ነገሥታት ስጦታ ያቅርቡለት፤ የሳባና የዐረብ ነገሥታት እጅ መንሻ ያምጡለት።


በምሥራቅ ነፋስ እንደሚሰባበሩ የተርሴስ መርከቦች ሆኑ።


የያዋን ልጆች፦ የኤሊሻ፥ የተርሴስ፥ የኪቲምና የሮዳኒም ሰዎች ናቸው።


በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፤ ከሞት ከተረፉት መካከል ስለ እኔ ወዳልሰሙትና ክብሬንም ወዳላዩት ወደ ተለያዩ ሕዝቦች ወደ ተርሴስ፥ ወደ ሊብያውያን ቀስት ወደሚያስፈነጥሩ ወደ ሊድያውያን፥ ወደ ቱባል፥ ወደ ግሪክ፥ ራቅ ብለው ወደሚገኙት ደሴቶችም እልካቸዋለሁ፤ እነርሱም በሕዝቦች መካከል ክብሬን ይገልጣሉ።


የእስራኤል ቅዱስ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን ስላከበራችሁ ለእርሱ ክብር ሲሉ በተርሴስ መርከቦች መሪነት ልጆቻችሁን ከብራቸውና ከወርቃቸው ጋር ከሩቅ ቦታ ለማምጣት ደሴቶቹ እኔን ይጠባበቃሉ።


የተርሴስ ሕዝብ ሆይ! ከእንግዲህ ወዲያ ወደብ ስለሌላችሁ ልክ በአባይ ወንዝ ዳር እንደሚደረገው ምድራችሁን እረሱ።


እናንተ በባሕር ጠረፍ የምትኖሩ ሕዝብ ሆይ! በዋይታ እያለቀሳችሁ ወደ ተርሴስ ተሻገሩ።


ስለ ጢሮስ ከተማ የተነገረ የትንቢት ቃል ይህ ነው፤ ጢሮስና ቤትዋ ወይም ወደብዋ የፈራረሱ ስለ ሆነ እናንተ የተርሴስ መርከቦች እሪ በሉ፤ ከቆጵሮስ ስትመለሱ የሚጠብቃችሁ ወሬ ይኸው ነው።


እጅግ የተዋቡ ዕቃዎችንና የተርሴስ መርከቦችን እንኳ ያሰጥማል፤


ሰሎሞንም በኪራም አገልጋዮች አማካይነት ወደ ተርሴስ የሚጓዙ መርከቦች ነበሩት፤ እነርሱም በየሦስት ዓመቱ ወርቅን፥ ብርን፥ የዝሆን ጥርስን፥ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር።


ዮናስ ግን ከእግዚአብሔር ፊት ለመኰብለል አስቦ ወደ ተርሴስ ለመሄድ ተነሣ፤ ወደ ኢዮጴም ወርዶ ከዚያ ወደ ተርሴስ የምትጓዝ መርከብ አገኘ፤ ለጒዞ የሚያስፈልገውንም ዋጋ ከከፈለ በኋላ ወደ መርከቢቱ ገባ፤ ሐሳቡም ከእግዚአብሔር ለመሸሽ ነበር።


የክረምቱንና የበጋውን ወራት የሚያሳልፉባቸውን ቤቶች ሁሉ እደመስሳለሁ፤ በዝሆን ጥርስ አጊጠው የተሠሩ ቤቶች ሁሉ ይፈርሳሉ፤ ታላላቅ ቤቶች ሁሉ ይወድማሉ።”


“ከብልጽግናሽ ብዛት የተነሣ ከተርሴስ ጋር ንግድ በመለዋወጥ በአንቺ ዕቃዎች ለውጥ ከእርስዋ ብር፥ ብረት፥ ቆርቆሮና እርሳስ ታገኚ ነበር።


“ሰጎን ክንፎችዋን በፍጥነት ትዘረጋለች፤ ነገር ግን እንደ ሸመላ አትበርም።


እንዲሁም ንጉሥ ሰሎሞን ከዝሆን ጥርስ አንድ ትልቅ ዙፋን አሠርቶ በንጹሕ ወርቅ አስለበጠው፤


እንዲሁም ንጉሥ ሰሎሞን በኤዶም ምድር በቀይ ባሕር ዳርቻ በምትገኘው በኤላት አጠገብ ባለችው በዔጽዮንጋብር መርከቦችን ሠራ።


በሰሎሞን ዘመን ብር ምንም ዋጋ ስላልነበረው ሰሎሞን የሚጠጣባቸው ዋንጫዎች ሁሉና “የሊባኖስ ደን” ተብሎ በሚጠራው አዳራሽ ውስጥ የሚገኙት ዕቃዎች በሙሉ ከንጹሕ ወርቅ እንጂ ከብር አልተሠሩም፤


ከሮድ አገር ሰዎች ጋር የንግድ ሥራ ታካሂጂ ነበር፤ በባሕር ዳር የሚገኙ አገሮች ሕዝቦች ሸቀጥሽን ወስደው በምትኩ የዝሆን ጥርስና ዞጲ ያመጡልሽ ነበር።


ከዚያም በኋላ የእስራኤል ንጉሥ አካዝያስ መርከበኞቹ ከኢዮሣፍጥ መርከበኞች ጋር በኅብረት እንዲሠሩ የውል ድርድር አቅርቦ ነበር፤ ኢዮሣፍጥ ግን ሐሳቡን አልተቀበለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios