Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 1:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ቤርሳቤህም እንዲህ ስትል መለሰች፤ “ጌታዬ ሆይ! ልጄ ሰሎሞን የዙፋንህ ወራሽ ሆኖ እንደሚነግሥና በዙፋንህ እንደሚቀመጥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ስም ምለህ ቃል ገብተህልኝ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እርሷም እንዲህ አለችው፣ “ጌታዬ ሆይ፤ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ ቀጥሎ ይነግሣል፤ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለህ አንተው ራስህ ለአገልጋይህ በአምላክህ በእግዚአብሔር ምለህልኝ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እርሷም አለችው፦ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ለባርያህ፦ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፥ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለህ በጌታ በእግዚአብሔር ምለህልኛል፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እር​ስ​ዋም አለ​ችው፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ አንተ ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ፦ ልጅሽ ሰሎ​ሞን ከእኔ በኋላ ይነ​ግ​ሣል፤ በዙ​ፋ​ኔም ይቀ​መ​ጣል ብለህ በአ​ም​ላ​ክህ ምለ​ህ​ልኝ አል​ነ​በ​ረ​ምን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እርስዋም አለችው “ጌታዬ ሆይ! አንተ ለባሪያህ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፤ በዙፋኔም ይቀመጣል፤’ ብለህ በአምላክህ በእግዚአብሔር ምለህልኛል፤

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 1:17
7 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ሣራ “እኔ አሁን እንዲህ ካረጀሁ በኋላ ጌታዬ አብርሃምም ካረጀ በኋላ እንዲህ ያለ ደስታ ሊኖረኝ ይችላልን?” ብላ በማሰብ ሳቀች።


ወደ ንጉሥ ዳዊት ገብተሽ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ነግሦ በዙፋኔ ይቀመጣል’ ብለህ ለአገልጋይህ በመሐላ ቃል ገብተህልኝ አልነበረምን? ታዲያ፥ አሁን አዶንያስ እንዴት ሊነግሥ ቻለ? ብለሽ ንገሪው”።


“ከንጉሥ ዳዊት ጋር በምትነጋገሪበት ጊዜ እኔም ወዲያውኑ ገብቼ አንቺ የተናገርሺው ሁሉ እውነት መሆኑን አረጋግጣለሁ” አላት።


ቤርሳቤህም ወደ መሬት ለጥ ብላ እጅ ነሣች፤ ንጉሡም “ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት።


አሁን ግን ጌታዬ ንጉሡ ሳታውቅ አዶንያስ ነግሦአል።


ልጅሽ ሰሎሞን በእኔ እግር ተተክቶ እንደሚነግሥ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ስም ከዚህ በፊት የገባሁልሽን ቃል በዛሬው ዕለት የምፈጽም መሆኔን አረጋግጥልሻለሁ።”


የታዘዙትም ሣራ አብርሃምን “ጌታዬ!” እያለች ትታዘዝለት እንደ ነበረው ዐይነት ነው፤ እናንተም መልካም የሆነውን ነገር ብታደርጉና አንዳች የሚያስፈራ ነገር ባያስደነግጣችሁ የእርስዋ ልጆች ናችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos