1 ቆሮንቶስ 7:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም39 ሚስት ባልዋ በሕይወት እስካለ ድረስ በጋብቻ ሕግ የታሰረች ናት፤ ባልዋ ከሞተ ግን የፈለገችውን ለማግባት ነጻ ነች፤ ሆኖም የምታገባው ሰው ክርስቲያን መሆን አለበት። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም39 አንዲት ሴት ባሏ በሕይወት እስካለ ድረስ ከርሱ ጋራ የታሰረች ናት፤ ባሏ ቢሞት ግን፣ የፈለገችውን ሰው ለማግባት ነጻነት አላት፤ ሰውየው ግን በጌታ መሆን አለበት። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)39 ሚስት ባሏ በሕይወት እስካለ የታሰረች ናት፤ ባሏ ቢሞት ግን በጌታ ይሁን እንጂ የወደደችውን ልታገባ ነጻነት አላት። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)39 ሴት ባልዋ በሕይወት ሳለ የታሠረች ናት፤ ባልዋ የሞተ እንደ ሆነ ግን ነጻ ናት፤ የወደደችውን ታግባ፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ይሁን። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)39 ሴት ባልዋ በሕይወት ሳለ የታሰረች ናት፤ ባልዋ ቢሞት ግን በጌታ ይሁን እንጂ የወደደችውን ልታገባ ነጻነት አላት። Ver Capítulo |