Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 6:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከእናንተ አንዱ ክርስቲያን ከሆነው ወንድሙ ጋር ቢጣላ ጉዳዩን ክርስቲያኖች በፍርድ እንዲያዩለት በማድረግ ፈንታ ለክስ ወደ አሕዛብ የፍርድ ሸንጎ ለመሄድ እንዴት ይደፍራል?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከመካከላችሁ አንድ ሰው ከሌላው ጋራ ሙግት ቢኖረው፣ ጕዳዩን በቅዱሳን ፊት በማቅረብ ፈንታ እንዴት ደፍሮ በዐመፀኞች ፊት ለመፋረድ ያቀርባል?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ከእናንተ አንዱ ከባልንጀራው ጋር ጥል ቢኖረው በቅዱሳን ፊት በመፋረድ ፋንታ በአሕዛብ ፊት ሊፋረድ እንዴት ይደፍራል?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እን​ግ​ዲህ በሚ​ነ​ቅፉ ሰዎች ዘንድ ልት​ከ​ራ​ከሩ አት​ድ​ፈሩ፤ ከጓ​ደ​ኛው ጋር በዐ​መ​ፀ​ኞች ዘንድ ሊከ​ራ​ከር የሚ​ችል አለን? በደ​ጋ​ጎች ዘንድ አይ​ደ​ለ​ምን? ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ጋር ክር​ክር ያለው ቢኖ​ርም በቅ​ዱ​ሳን ዘንድ ይከ​ራ​ከር፤ በሚ​ነ​ቅ​ፉና በዐ​መ​ፀ​ኞች ዘንድ ግን አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ከእናንተ አንዱ ከባልንጀራው ጋር ሙግት ቢኖረው በቅዱሳን ፊት በመፋረድ ፋንታ በዓመፀኞች ፊት ሊፋረድ ይደፍራልን?

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 6:1
11 Referencias Cruzadas  

ይህን ብታደርጉ፥ በሰማይ ላለው አባታችሁ ልጆች ትሆናላችሁ። እርሱ ለክፉዎችና ለደጎች ፀሐዩን ያወጣል፤ እንዲሁም ለጻድቃንና ለግፈኞች ዝናቡን ያዘንባል።


ድሜጥሮስና ከእርሱ ጋር ያሉት አንጥረኞች የሚከሱት ሰው ካለ ፍርድ የሚሰጥባቸው ቀኖች አሉ፤ ባለሥልጣኖችም አሉ፤ እዚያ ይሟገቱ።


በቆሮንቶስ ከተማ ለምትገኘው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ በውስጥዋም በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱትና ቅዱሳን እንዲሆኑ ለተጠሩት፥ እንደዚሁም በየቦታው ለእነርሱና ለእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ለሚጠሩት ሁሉ።


በእግዚአብሔር ሕዝብ አብያተ ክርስቲያን ሁሉ ዘንድ እንደሚደረገው እግዚአብሔር የሰላም አምላክ ነው እንጂ የሁከት አምላክ አይደለም።


ለምእመናን ስለሚደረገው የገንዘብ መዋጮ ለገላትያ አብያተ ክርስቲያን በሰጠሁት መመሪያ መሠረት እናንተም እንዲሁ አድርጉ።


ወንድሞች ሆይ! የእስጢፋኖስ ቤተሰብ በአካይያ አገር የመጀመሪያዎቹ አማኞች እንደ ሆኑና ምእመናንን ለማገልገል ራሳቸውን አሳልፈው እንደ ሰጡ ታውቃላችሁ።


ከክርስቲያናዊ ማኅበር ውጪ ባሉት ሰዎች ላይ ለመፍረድ እኔ ማን ነኝ? በክርስቲያናዊ ማኅበር ውስጥ ስላሉት ሰዎች ጉዳይ እናንተስ መፍረድ ትችሉ የለምን?


ይህን የምለው እንድታፍሩ ብዬ ነው፤ ኧረ ለመሆኑ በወንድሞች መካከል ውሳኔ ለመስጠት የሚችል አስተዋይ ሽማግሌ አይገኝምን?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos