Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 5:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በምትሰበሰቡበት ጊዜ እኔም በጌታችን በኢየሱስ ኀይል በመካከላችሁ በመንፈስ ስለምገኝ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በምትሰበሰቡበት ጊዜ እኔም በመንፈስ ከእናንተ ጋራ ስለምሆን፣ በጌታችን በኢየሱስ ስምና በመካከላችሁ በሚገኘው በጌታችን በኢየሱስ ኀይል፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ጋር፥ በጌታችን ኢየሱስ ስም ተሰብስባችሁ፥ መንፈሴም አብሮችሁ ነው፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ተሰ​ብ​ስ​ባ​ችሁ፥ በእኔ ሥል​ጣን፥ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱ​ስም ኀይል፥

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 5:4
18 Referencias Cruzadas  

በኢየሱስ በኩል እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ በቃልም ሆነ በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት፤ በእርሱም እግዚአብሔር አብን አመስግኑ።


እናንተ በእኔ ዐድሮ የሚናገረው ክርስቶስ መሆኑን ለማረጋገጥ ትፈልጋላችሁ፤ በእናንተ ዘንድ የሚታየውም የእርሱ ኀይል ነው እንጂ ድካሙ አይደለም።


እናንተ የሰዎችን ኃጢአት ይቅር ብትሉ ይቅር ይባልላቸዋል፤ እናንተ የሰዎችን ኃጢአት ይቅር ባትሉ ግን፥ ይቅር አይባልላቸውም” አላቸው።


ወንድሞች ሆይ! ሥራ ፈት ከሆነውና ከእኛ በተላለፈላችሁ ትውፊት መሠረት ከማይኖር ክርስቲያን ሁሉ እንድትለዩ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።


እነሆ፥ ለአንተ የሰማይ መንግሥትን መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር ያሰርከው በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤ በምድር የፈታኸው በሰማይ የተፈታ ይሆናል።”


በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ሁሉ ነገር እግዚአብሔር አብን ዘወትር አመስግኑ።


ይህን መልእክት ከእናንተ ርቄ ሳለሁ የጻፍኩላችሁ በዚሁ ምክንያት ነው፤ በዚህ ዐይነት ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ጌታም በሰጠኝ ሥልጣን አላስጨንቃችሁም፤ ጌታ ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ እናንተን ለማፍረስ አይደለም።


ይህንንም ብዙ ቀን እየደጋገመች ታደርግ ነበር፤ ጳውሎስ ግን ተበሳጨና ዞር ብሎ ርኩሱን መንፈስ “በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ከእርስዋ እንድትወጣ አዝሃለሁ!” አለው። ርኩሱም መንፈስ ወዲያውኑ ወጣ።


ጴጥሮስ ግን “ብርና ወርቅ የለኝም፤ ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሥና ተራመድ!” አለው።


ያዘዝኳችሁንም ሁሉ እንዲፈጽሙ አስተምሩአቸው! እነሆ፥ እኔም እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”


ኢየሱስ ወደ እነርሱ ቀረበና እንዲህ አላቸው፤ “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል፤


ሁለት ወይም ሦስት ሆነው በስሜ በሚሰበሰቡበት ስፍራ እኔ በመካከላቸው እገኛለሁ።”


በቅዱሱ ልጅህ በኢየሱስ ስም በሽተኞች እንዲድኑና ተአምራትም፥ ድንቅ ነገሮችም እንዲደረጉ እጅህን ዘርጋ።”


ለእንዲህ ዐይነቱ ሰው ከእናንተ አብዛኞቹ የፈረዱበት ቅጣት ይበቃዋል።


እነርሱም የሮቤል፥ የጋድና በምሥራቅ የሚኖሩት የምናሴ ሕዝብ ወደሚኖሩባት ወደ ገለዓድ ምድር መጥተው እንዲህ አሉአቸው፦


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios