Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 15:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እኔ ያስተማርኳችሁን የወንጌል ቃል አጥብቃችሁ ብትይዙ በእርሱ ትድናላችሁ፤ አለበለዚያ ግን ያመናችሁት በከንቱ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የሰበክሁላችሁን ቃል አጥብቃችሁ ብትይዙ፣ በዚህ ወንጌል ትድናላችሁ፤ አለዚያ ያመናችሁት በከንቱ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የሰበክሁላችሁን ቃል አጥብቃችሁ ብትይዙ፥ ያመናችሁት በከንቱ ካልሆነ በስተቀር፥ የምትድኑበትን ወንጌል ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ያስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ች​ሁን ታስቡ እንደ ሆነ በቃሌ አስ​ተ​ም​ሬ​አ​ች​ኋ​ለሁ፤ ያለ​ዚያ ግን ማመ​ና​ችሁ ከንቱ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በከንቱ ካላመናችሁ በቀር፥ ብታስቡት፥ በምን ቃል እንደ ሰበክሁላችሁ አሳስባችኋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 15:2
31 Referencias Cruzadas  

ክርስቶስ ግን በእግዚአብሔር ቤት ታማኝ የሆነው እንደ ልጅ ሆኖ ነው፤ ቤቱም እኛ ነን፤ ቤቱ የምንሆነውም የምንተማመንበትን ነገርና የምንመካበትን ተስፋ አጽንተን ስንይዝ ነው።


ስለዚህ ከሰማነው ነገር ተንሸራትተን እንዳንወድቅ ስለ ሰማነው ነገር በጣም መጠንቀቅ አለብን።


በመጀመሪያ የነበረንን እምነታችንን እስከ መጨረሻ አጽንተን ከያዝን ከክርስቶስ ጋር ወራሾች እንሆናለን።


እርሱ እኛ ስላደረግነው መልካም ሥራ ሳይሆን በራሱ ፈቃድና በጸጋው አዳነን፤ ለቅድስናም ጠራን፤ ይህንንም ጸጋ ከዘመናት በፊት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሰጠን።


ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በወንጌሉ ከተገኘው ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት ጸንታችሁ ስትኖሩ ብቻ ነው፤ ይህም ወንጌል እናንተ የሰማችሁትና በዓለም ላይ ላሉት ሰዎች ሁሉ የተሰበከ ነው፤ እኔ ጳውሎስም አገልጋይ የሆንኩት ለዚሁ ወንጌል ነው።


እናንተ የዳናችሁት በእምነት አማካይነት በጸጋው ነው፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ በእናንተ ሥራ የተገኘ አይደለም።


የመስቀሉ ነገር ለሚጠፉት ሰዎች እንደ ሞኝነት ይቈጠራል፤ ለምንድን ለእኛ ግን የእግዚአብሔር ኀይል ነው።


አካል ያለ ነፍስ የሞተ ነው፤ እንዲሁም ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።


ወንድሞቼ ሆይ! ሰው እምነት አለኝ ቢል፥ ነገር ግን እምነቱን በመልካም ሥራ ባይገልጥ ምን ይጠቅመዋል? እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን?


የተስፋውን ቃል የሰጠን ታማኝ ስለ ሆነ አሁን አምነን የምንመሰክረውን ተስፋ ሳናወላውል አጥብቀን እንያዝ።


በጭንጫማ መሬት ላይ የወደቀውም ዘር የሚያመለክተው ቃሉን ሰምተው በደስታ የሚቀበሉትን ሰዎች ነው፤ ነገር ግን እነርሱ የሚያምኑት ለጊዜው ነው፤ ሥር ስለሌላቸውም በፈተና ጊዜ ወዲያውኑ ይክዳሉ።


ከመልካም ሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።


እንግዲህ ሰማያትን ዘልቆ ወደ ላይ ወደ ሰማይ የወጣ ታላቅ የካህናት አለቃ ስላለን እምነታችንን አጥብቀን እንያዝ፤ የካህናት አለቃውም የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነው።


ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በቃላችንም ሆነ በመልእክታችን ከእኛ የተላለፈላችሁን ትምህርት አጥብቃችሁ ያዙ።


በወንጌል ምክንያት የተቀበላችሁት መከራ ሁሉ ከንቱ ሆኖ ቀረ ማለት ነውን? ይህን አድርጋችሁ ከሆነ በእርግጥ ከንቱ ሆኖ ቀርቶአል።


ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ እንደ መሆናችን የተቀበላችሁትን ጸጋ በከንቱ አታስቀሩት ብለን እንለምናችኋለን።


እኔ በወንጌል ቃል አላፍርም፤ የወንጌል ቃል በመጀመሪያ አይሁድን፥ ቀጥሎም አሕዛብን፥ እንዲሁም የሚያምኑትን ሰዎች ሁሉ ማዳን የሚችል የእግዚአብሔር ኀይል ነው።


የተማርከው ትምህርት ሕይወትን ስለሚሰጥህ አጥብቀህ ያዘው፤ አትተወው፤ ደኅና አድርገህም ጠብቀው።


ልጄ ሆይ! የማስተምርህን አትርሳ፤ ትእዛዞቼንም በልብህ ጠብቅ።


እኛ ለሚድኑትም ሆነ ለሚጠፉት መልካም ሽታ እንዳለው ዕጣን በክርስቶስ ለእግዚአብሔር የቀረብን ነን።


ክርስቶስ ከሞት ካልተነሣ የእኛም ትምህርት ሆነ የእናንተም እምነት ከንቱ መሆኑ ነው፤


የዚህ ዓለም ሰዎች በገዛ ጥበባቸው እግዚአብሔርን ማወቅ እንዳይችሉ እግዚአብሔር በጥበቡ ዘጋባቸው፤ ነገር ግን እንደ ሞኝነት በሚቈጠረው እኛ በምናስተምረው ወንጌል የሚያምኑትን ለማዳን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖአል።


እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቸርነትና አስፈሪነት ተመልከቱ፤ አስፈሪነቱን የሚያሳየው በወደቁት ላይ ሲሆን ቸርነቱን የሚያሳየው ግን ለእናንተ ነው፤ ይህንንም የሚያደርገው እርሱን በማመን ጸንታችሁ ብትኖሩ ነው፤ ባትጸኑ ግን እናንተም ተቈርጣችሁ ትወድቃላችሁ።


ስምዖን እንኳን ሳይቀር አምኖ ተጠመቀና ከፊልጶስ ጋር ተባባሪ ሆነ፤ የሚደረጉትንም ድንቅ ነገሮችና ታላላቅ ተአምራት በማየቱ ይገረም ነበር።


ጌታንም ያመሰግኑ ነበር፤ ሰውም ሁሉ ያከብራቸው ነበር፤ እግዚአብሔርም የሚድኑትን ሰዎች በየቀኑ ወደ ማኅበራቸው ይጨምር ነበር።


እውነትን፥ ጥበብን፥ ተግሣጽን፥ ማስተዋልን ገንዘብ አድርጋቸው እንጂ አትተዋቸው።


ዘወትር ስለምታስታውሱኝና የሰጠኋችሁንም ትውፊት አጥብቃችሁ ስለ ያዛችሁ፥ አመሰግናችኋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios