Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 1:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ታዲያ ክርስቶስ ተከፋፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቅሎአልን? ወይስ የተጠመቃችሁት በጳውሎስ ስም ነውን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ለመሆኑ ክርስቶስ ተከፍሏልን? ጳውሎስስ ለእናንተ ተሰቅሏልን? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠምቃችኋልን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቅሎአልን? ወይስ የተጠመቃችሁት በጳውሎስ ስም ነበር?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ክር​ስ​ቶስ ተከ​ፍ​ሎ​አ​ልን? ወይስ በውኑ ጳው​ሎስ ስለ እና​ንተ ተሰ​ቅ​ሎ​አ​ልን? ወይስ በጳ​ው​ሎስ ስም ተጠ​ም​ቃ​ች​ኋ​ልን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቀለን? ወይስ በጳውሎስ ስም ተጠመቃችሁን?

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 1:13
15 Referencias Cruzadas  

እንዲሁም አንድ ጌታ፥ አንድ እምነትና አንድ ጥምቀት አለ።


አንድ ሰው ወደ እናንተ መጥቶ እኛ የሰበክነውን ሳይሆን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክላችሁ ወይም እናንተ የተቀበላችሁትን መንፈስ ሳይሆን ሌላ መንፈስ ብትቀበሉ፥ ወይም የተቀበላችሁትን ወንጌል ሳይሆን ሌላ ወንጌል ብትቀበሉ፥ ዝም ብላችሁ ተሸነፋችሁ ማለት ነው።


ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፤ “ንስሓ ግቡ፤ ኃጢአታችሁም ይቅር እንዲባልላችሁ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የእግዚአብሔር ስጦታ የሆነውን መንፈስ ቅዱስንም ትቀበላላችሁ፤


የሙሴ ተባባሪዎች ለመሆንም በዚህ ደመናና በዚህ ባሕር ተጠመቁ።


ይህን በሰሙ ጊዜ በጌታ በኢየሱስ ስም ተጠመቁ።


ስለዚህ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እንዲጠመቁ አዘዘ፤ ከዚህ በኋላ ጴጥሮስ ከእነርሱ ጋር ለጥቂት ቀኖች እንዲቈይ ለመኑት።


ይህንንም ያልኩት ግራ የሚያጋቡአችሁና የክርስቶስንም ወንጌል ለማጣመም የሚፈልጉ አንዳንድ ሰዎች ስላሉ ነው እንጂ ወንጌልማ በመሠረቱ አንድ ብቻ ነው።


እንግዲህ ወደ ዓለም ሕዝብ ሁሉ ሂዱ፤ በአብ፥ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው የእኔ ደቀ መዛሙርት አድርጉአቸው።


ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።


ስለዚህ “በእኔ በጳውሎስ ስም ተጠምቃችኋል” ብሎ መናገር የሚችል የለም።


ስለዚህ ክርስቶስ ሞቶ ከሞት የተነሣው የሕያዋንና የሙታን ጌታ ለመሆን ነው።


የሰማርያ ሰዎች በጌታ ኢየሱስ ስም ተጠምቀው ነበር እንጂ መንፈስ ቅዱስ ገና በአንዳቸውም ላይ አልወረደም ነበር።


ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ፥ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ይጠመቁ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios