Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 3:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ፈዳያም ዘሩባቤልና ሺምዒ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ዘሩባቤልም መሹላምና ሐናንያ ተብለው የሚጠሩ ሁለት ወንዶች ልጆችና ሰሎሚት ተብላ የምትጠራ ሴት ልጅ ነበሩት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 የፈዳያ ወንዶች ልጆች፤ ዘሩባቤል፣ ሰሜኢ። የዘሩባቤል ወንዶች ልጆች፤ ሜሱላም፣ ሐናንያ፤ እኅታቸው ሰሎሚት ትባላለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የፈዳያ ልጆች ዘሩባቤልና ሰሜኢ ነበሩ፤ የዘሩባቤልም ልጆች፤ ሜሱላም፥ ሐናንያ፥ እኅታቸውም ሰሎሚት ነበረች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የፈ​ዳ​ያም ልጆች ዘሩ​ባ​ቤ​ልና ሰሜኤ ነበሩ፤ የዘ​ሩ​ባ​ቤ​ልም ልጆች፤ ሜሱ​ላም፥ ሐና​ንያ፥ እኅ​ታ​ቸ​ውም ሰሎ​ሚት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የፈዳያ ልጆች ዘሩባቤልና ሰሜኢ ነበሩ፤ የዘሩባቤልም ልጆች፤ ሜሱላም፥ ሐናንያ፥ እኅታቸውም ሰሎሚት።

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 3:19
10 Referencias Cruzadas  

እንዲሁም ሌሎች አምስት ወንዶች ልጆች ሲኖሩት፥ እነርሱም ሐሹባ፥ ኦሔል፥ ቤሬክያ፥ ሐሳድያና ዩሻብሔሴድ ተብለው የሚጠሩ ናቸው።


ለተመለሱትም ስደተኞች መሪዎች ሆነው የመጡት ዘሩባቤል፥ ኢያሱ፥ ነህምያ፥ ሠራያ፥ ረዔላያ፥ መርዶክዮስ፥ ቢልሻን፥ ሚስፓር፥ ቢግዋይ፥ ሬሁምና በዓና ተብለው የሚጠሩት ነበሩ። ከእያንዳንዱ እስራኤላዊ ጐሣ በመሰባሰብ ወደ ሀገር የተመለሱትም ስደተኞች ዝርዝር ከዚህ የሚከተለው ነው፦


የኢዮጼዴቅ ልጅ ኢያሱም ከወገኖቹ ካህናትና የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤልም ከዘመዶቹ ጋር በመተባበር የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን መሠዊያ እንደገና ሠሩ፤ የእግዚአብሔር ሰው ለሆነው ለሙሴ በተሰጠው የሕግ መጽሐፍ በተጻፈውም መመሪያ መሠረት በዚያ መሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ለማቅረብ ቻሉ።


ዳርዮስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፥ ስድስተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን፥ እግዚአብሔር በነቢዩ አማካይነት በሐጌ ተናገረ የተናገረውም የይሁዳ ገዢ ለነበረው ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤልና ሊቀ ካህናት ለነበረው ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለኢያሱ ነው።


ጌታ ይሁዳ ገዢ ለሆነው ለሰላትያል ልጅ ለዘሩባቤል፥ ሊቀ ካህናት ለሆነው ለኢዮሴዴቅ ልጅ ለኢያሱና ተርፎ ከስደት ለተመለሰው ሕዝብ እንዲህ ብለህ ተናገር አለው።


አሁን ግን ዘሩባቤል ሆይ! በርታ ሊቀ ካህናቱ የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ሆይ! በርታ፤ የሀገሪቱ ሕዝብ ሆይ! በርቱ! እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ። እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ።


ከባቢሎን ምርኮ በኋላ ኢኮንያን ሰላትያልን ወለደ፤ ሰላትያል ዘሩባቤልን ወለደ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos