Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 24:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7-18 ኻያ አራቱ የቤተሰብ ቡድኖች በዕጣ የወጣላቸው የሥራ ምድቡ ክፍፍል ቅደም ተከተል ተራ እንደሚከተለው ነው፦ አንደኛ በይሆያሪብ የሚመራው ቡድን፥ ሁለተኛ በይዳዕያ የሚመራው ቡድን፥ ሦስተኛ በሐሪም የሚመራው ቡድን፥ አራተኛ በሰዖሪም የሚመራው ቡድን፥ አምስተኛ በማልኪያ የሚመራው ቡድን፥ ስድስተኛ በሚያሚን የሚመራው ቡድን፥ ሰባተኛ በሀቆጽ የሚመራው ቡድን፥ ስምንተኛ በአቢያ የሚመራው ቡድን፥ ዘጠነኛ በኢያሱ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥረኛ በሸካንያ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ አንደኛ በኤልያሺብ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ ሁለተኛ በያቂም የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ ሦስተኛ በሑፓ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ አራተኛ በዬሼብአብ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ አምስተኛ በቢልጋ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ ስድስተኛ በኢሜር የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ ሰባተኛ በሔዚር የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ ስምንተኛ በሃፒጼጽ የሚመራው ቡድን፥ ዐሥራ ዘጠነኛ በፐታሕያ የሚመራው ቡድን፥ ኻያኛ በይሔዝቄል የሚመራው ቡድን፥ ኻያ አንደኛ በያኪን የሚመራው ቡድን፥ ኻያ ሁለተኛ በጋሙል የሚመራው ቡድን፥ ኻያ ሦስተኛ በደላያ የሚመራው ቡድን፥ ኻያ አራተኛ በማዓዝያ የሚመራው ቡድን።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የመጀመሪያው ዕጣ ለዮአሪብ፣ ሁለተኛውም ዕጣ ለዮዳሄ ወጣ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 መጀመሪያውም ዕጣ ለዮአሪብ ወጣ፥ ሁለተኛው ለዮዳኤ፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 መጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ዕጣ ለኢ​ያ​ሬብ ወጣ፤ ሁለ​ተ​ኛ​ውም ለኢ​ያ​ድያ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 መጀመሪያውም ዕጣ ለዮአሪብ ወጣ፥ ሁለተኛው ለዮዳኤ፥

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 24:7
7 Referencias Cruzadas  

ዕጣውንም በቅድሚያ ለማውጣት የአልዓዛርና የኢታማር ዘሮች ተራ ይገቡ ነበር፤ ከዚህም በኋላ በሌዋዊው ጸሐፊ በናትናኤል ልጅ በሸማዕያ ይመዘግቡ ነበር፤ ንጉሡና ባለሟሎቹ የሆኑት ባለሥልጣኖች፥ ካህናቱ ሳዶቅና የአብያታር ልጅ አቤሜሌክ፥ እንዲሁም የካህናትና የሌዋውያን ቤተሰቦች አለቆች ሁሉ ምስክሮች ነበሩ።


በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩት ካህናት የሚከተሉት ናቸው፦ ይዳዕያ፥ ይሆያሪብና ያኪን፤ በቤተ መቅደስ ዋና ባለሥልጣን የሆነው የሒልቂያ ልጅ ዐዛርያስ፤ የእርሱም የቀድሞ አባቶች መሹላም፥ ጻዶቅ፥ መራዮትና አሒጡብ ናቸው። የይሮሐም ልጅ ዐዳያ፤ የእርሱም የቀድሞ አባቶች ፓሽሑር ማልኪያ ናቸው። የዐዲኤል ልጅ ማዕሳይ፤ የእርሱም የቀድሞ አባቶች ያሕዜራ፥ መሹላም፥ መሺሌሚትና ኢሜር ናቸው።


ከዚህ የሚከተለው ደግሞ ከምርኮ የተመለሱ የካህናት ቤተሰብ ዝርዝር ነው፦ የኢያሱ ዘር የሆነው የይዳዕያ ቤተሰብ 973 የኢሜር ቤተሰብ 1052 የፓሽሑር ቤተሰብ 1247 የሓሪም ቤተሰብ 1017


ካህናት፦ ይዳዕያ የዩያሪብ ልጅ፥ የያኪን ልጁ፥


ከምርኮ የተመለሱ የካህናት ጐሣዎች ስም ዝርዝር ይህ ነው፦ የኢያሱ ዘር ከሆነው ከይዳዕያ ወገን 973 ከኢሜር ወገን 1052 ከፓሽሑር ወገን 1247 ከሓሪም ወገን 1017


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos