1 ዜና መዋዕል 11:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 ከሠላሳዎቹ መካከል እጅግ ታዋቂ ቢሆንም በዝነኛነቱ ከሦስቱ ኀያላን ጀግኖች ደረጃ አልደረሰም፤ ዳዊትም በናያን የክብር ዘብ አዛዥ በማድረግ ሾሞት ነበር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 ከሠላሳዎቹም ይልቅ የበለጠ ክብር ተጐናጸፈ፤ ይሁን እንጂ ከሦስቱ አንዱ አልነበረም፤ ዳዊትም የክብር ዘቡ አዣዥ አደረገው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 እነሆ፥ ከሠላሳው ይልቅ የከበረ ነበረ፥ ነገር ግን ወደ ፊተኞቹ ወደ ሦስቱ አልደረሰም። ዳዊትም በዘበኞቹ ላይ ሾመው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 እነሆ፥ ከሠላሳው ይልቅ የከበረ ነበረ፤ ነገር ግን ወደ ፊተኞቹ ወደ ሦስቱ አልደረሰም። ዳዊትም በናያስን በሀገሩ ላይ ሾመው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 እነሆ፥ ከሠላሳው ይልቅ የከበረ ነበረ፤ ነገር ግን ወደ ፊተኞቹ ወደ ሦስቱ አልደረሰም። ዳዊትም በዘበኞቹ ላይ ሾመው። Ver Capítulo |
ከሠላሳዎቹ መካከል የሌሎቹ ሰዎች ስም ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ የኢዮአብ ወንድም ዐሣሄል፥ የቤተልሔሙ ተወላጅ የዶዶ ልጅ ኤልሐናን፥ የሐሮድ ተወላጅ ሻሞት፥ የፌሌጥ ተወላጅ የሆነው ሔሌጽ፥ የተቆዓ ተወላጅ የሆነው የዒቄሽ ልጅ ዒራ፥ የዐናቶት ተወላጅ የሆነው አቢዔዜር፥ የሑሻ ተወላጅ የሆነው ሲበካይ፥ የአሖሕ ተወላጅ የሆነው ዒላይ፥ የነጦፋ ተወላጅ የሆነው ማህራይ፥ የነጦፋ ተወላጅ የሆነው የባዕና ልጅ ሔሌድ፥ በብንያም ግዛት የምትገኘው የጊብዓ ተወላጅ የሪባይ ልጅ ኢታይ፥ የፒርዓቶን ተወላጅ የሆነው በናያ፥ በጋዓሽ አጠገብ ባሉት ሸለቆዎች የተወለደው ሑራይ፥ የዓረባ ተወላጅ የሆነው አቢኤል፥ የባሕሩም ተወላጅ የሆነው ዓዝማዌት፥ የሻዓልቦን ተወላጅ የሆነው ኤልያሕባ፥ የጊዞን ተወላጅ የሆነው ሃሼም፥ የሃራር ተወላጅ የሆነው የሻጌ ልጅ ዮናታን፥ የሀራር ተወላጁ የሳካር ልጅ አሒአም፥ የኡር ልጅ ኤሊፋል፥ የመኬራ ተወላጅ የሆነው ሔፌር፥ የፐሎን ተወላጅ የሆነው አሒያ፥ የቀርሜሎስ ተወላጅ የሆነው ሔጽሮ፥ የኤዝባይ ልጅ ናዕራይ፥ የናታን ወንድም ዮኤል፥ የሃግሪ ልጅ ሚብሐር፥ የዐሞን ተወላጅ የሆነው ጼሌቅ፥ የበኤሮት ተወላጅና የኢዮአብ ጋሻጃግሬ የነበረው ናሕራይ፥ የያቲር ተወላጆች የሆኑት ዒራና ጋሬብ፥ ሒታዊው ኦርዮን፥ የአሕላይ ልጅ ዛባድ፥ የሺዛ ልጅ ዐዲና፤ (ይህ ሰው የራሱ ቡድን የሆኑ ሠላሳ ወታደሮችን እንደ ያዘ ከሮቤል ነገድ የታወቀ ነበር፤) የማዕካ ልጅ ሐናን፥ የሚታን ተወላጅ የሆነው ኢዮሣፍጥ፥ የዐሽተራ ተወላጅ የሆነው ዑዚያ፥ የዓሮዔር ተወላጅ የሆነው የሆታም ልጆች ሻማዕና ይዒኤል፥ የቲጺ ተወላጅ የሆነው የሺምሪ ልጆች ይዲዕኤልና ዮሐ፥ የማሐዋ ተወላጅ የሆነው ኤሊኤል፥ የኤልናዓም ልጆች ይሪባይና ዮሻውያ፥ የሞአብ ተወላጅ የሆነው ዩትማ፥ የጾባ ተወላጆች የሆኑት ኤሊኤል፥ ዖቤድና ያዕሲኤል።