Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘካርያስ 8:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በዚህ ወራት በዚህ በተረፈው ሕዝብ ዐይን ነገሩ ቢያስደንቅ፥ በውኑ ለእኔ ግን አስደናቂ ይሆናልን? ይላል የሠራዊት ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እግዚአብሔር ጸባኦት እንዲህ ይላል፤ “በዚያ ጊዜ ይህ ለቀረው የእስራኤል ሕዝብ አስደናቂ መስሎ ሊታይ ይችላል፤ ለእኔ ግን አስደናቂ ሊሆን ይችላልን?” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “በእነዚህ ቀኖች ከሕዝቡ ለተረፉት ይህ የማይቻል ነገር ቢመስልም እንኳ በውኑ ለእኔ የማይቻል ነገር አለን?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህ ወራት በዚህ ሕዝብ ቅሬታ ዓይን ዘንድ ድንቅ ቢሆን፥ በውኑ በእኔ ዓይን ዘንድ ደግሞ ድንቅ ይሆናልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚህ ወራት በዚህ ሕዝብ ቅሬታ ዓይን ዘንድ ድንቅ ቢሆን፥ በውኑ በእኔ ዓይን ዘንድ ደግሞ ድንቅ ይሆናልን? ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ዘካርያስ 8:6
13 Referencias Cruzadas  

በውኑ ለጌታ የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፥ ሣራም ልጅን ታገኛለች።”


በዚህ ጊዜ የንጉሡ የቅርብ ባለሟል የሆነ አገልጋዩ ኤልሳዕን፥ “እግዚአብሔር ራሱ የሰማይ መስኮቶችን ከፍቶ እህልን እንደ ዝናብ ቢያዘንብ እንኳ ይህ ሊሆን ከቶ አይችልም!” ሲል በመጠራጠር ተናገረ። ኤልሳዕም “ያን እህል በዐይንህ ታያለህ፤ ነገር ግን ከእርሱ ምንም ነገር አትቀምስም!” አለው።


ይህች ከጌታ ዘንድ ሆነች፥ ለዓይናችንም ድንቅ ናት።


‘አቤቱ ጌታ ሆይ! ወዮ! እነሆ፥ በእውነት አንተ ሰማይንና ምድርን በታላቅ ኃይልህና በተዘረጋች ክንድህ ፈጥረሃል፥ ለአንተም ከቶ የሚሳንህ ምንም ነገር የለም።


እነሆ፥ እኔ የሥጋ ለባሽ ሁሉ አምላክ የሆንሁ ጌታ ነኝ፤ በውኑ ለእኔ የሚሳነኝ ነገር አለን?


ኢየሱስ ግን አያቸውና እንዲህ አላቸው “ይህ በሰው ዘንድ የማይቻል ነው፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ሁሉ ይቻላል።”


እነሆም፥ በጊዜያቸው የሚፈጸሙትን ቃሎቼን ስላላመንህ፥ ይህ ነገር እስከሚሆንበት ቀን ድረስ አንደበትህ ይታሰራል፤ መናገርም አትችልም፤” አለው።


ለእግዚአብሔር የሚሳነው አንዳች ነገር የለምና።”


እርሱ ግን “በሰው ዘንድ የማይቻል በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላል፤” አለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos