Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa መጽሐፈ ጦቢት 4:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ልጄ ሆይ ከዝሙት ተጠንቀቅ፥ ከሁሉ አስቀድመህ ከአባቶችህ ወገን የሆነች ሴት አግባ፥ እኛ የነቢያት ልጆች ነንና ከአባትህ ነገድ ያልሆነችውን ባዕድ ሴት አታግባ። ልጄ ሆይ ከጥንት ጀምሮ የነበሩትን አባቶቻችንን ኖኀን፥ አብርሃምን፥ ይስሐቅን፥ ያዕቆብን አስብ፤ ሁሉም ሚስት የወሰዱት ከወገኖቻቸው ነው፤ ስለዚህም በልጆቻቸውም የተባረኩ ሆኑ፤ ዘራቸውም ምድርን ይወርሳል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 “ልጄ! ራስህን ከዝሙት ጠብቅ፤ ከአባቶችህ ዘር ሁሉ አስቀድመህ ሚስት አግባ። ከዘመዶችህ ካልሆነች ከባዕድ ወገን ግን አታግባ። እኛ ከጥንት ጀምረው ከነበሩ ከነቢያት ከኖኅና ከአብርሃም ፥ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ልጆች ወገን ነንና፤ ልጄ ሆይ፥ ሁሉም ከአባቶቻቸው ትውልድ ሚስት እንዳገቡ አስብ፤ በልጆቻቸውም እንደ ተባረኩ፥ ዘሮቻቸውም ምድርን እንደ ወረሷት አስብ። Ver Capítulo |