Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ማሕልየ መሓልይ 5:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ፥ መቱኝ፥ አቈሰሉኝም፥ ቅጥር ጠባቂዎችም የዓይነ ርግብ መሸፈኛዬን ወሰዱት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የከተማዪቱም ጠባቂዎች፣ በከተማዪቱ ውስጥ ሲዘዋወሩ አገኙኝ፤ እነዚህ የቅጥሩ ጠባቂዎች፣ ደበደቡኝ፤ አቈሰሉኝ፤ ልብሴንም ገፈፉኝ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እየተዘዋወሩ ከተማውን የሚጠብቁ ሰዎች አገኙኝ፤ ደብድበውም አቈሰሉኝ፤ የከተማውን ቅጽር የሚጠብቁ ዘበኞች መጐናጸፊያዬን ገፈው ወሰዱብኝ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ከተ​ማ​ዪ​ቱን የሚ​ዞ​ሩት ጠባ​ቂ​ዎች አገ​ኙኝ፤ መቱኝ፥ አቈ​ሰ​ሉ​ኝም፤ ቅጥር ጠባ​ቂ​ዎ​ችም የዐ​ይነ ርግብ መሸ​ፈ​ኛ​ዬን ከራሴ ላይ ወሰ​ዱት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ፥ መቱኝ፥ አቈሰሉኝም፥ ቅጥር ጠባቂዎችም የዓይነ ርግብ መሸፈኛዬን ወሰዱት።

Ver Capítulo Copiar




ማሕልየ መሓልይ 5:7
25 Referencias Cruzadas  

ጻድቅ በጽኑ ፍቅር ይገሥጸኝ፥ ይዝለፈኝም፥ የክፉ ሰው ዘይት ግን ራሴን አይቀባ፥ ጸሎቴ ገና በክፋታቸው ላይ ነውና።


ከተማይቱን የሚዞሩት ጠባቂዎች አገኙኝ፥ ነፍሴ የወደደችውን አያችሁትን? አልኋቸውም።


ለውዴ ከፈትሁለት፥ ውዴ ግን ፈቀቅ ብሎ አልፎ ነበር። ነፍሴ ከመራቁ የተነሣ ደነገጠች፥ ፈለግሁት፥ አላገኘሁትም፥ ጠራሁት፥ ነገር ግን አልመለሰልኝም።


እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ አስምላችኋለሁ፥ ውዴን ያገኛችሁት እንደሆነ፥ እኔ ከፍቅር የተነሣ መታመሜን ንገሩት።


ለሰሎሞን በብኤላሞን የወይን ቦታ ነበረው፥ የወይኑን ቦታ ለጠባቂዎች አከራየው፥ ሰው ሁሉ ለፍሬው ሺህ ብር ያመጣለት ነበር።


መስታወቱን፤ ከጥሩ በፍታ የተሠራውን ልብስ፤ የራስ ጌጡን፤ ዐይነ ርግቡን ሁሉ ይነጥቃቸዋል።


ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ዘብ ጠባቂዎችን በቅጥሮችሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ ቀንም ሆነ ሌሊት ከቶ ዝም አይሉም። እናንት ወደ ጌታ አቤት፤ አቤት የምትሉ፤ ፈጽሞ አትረፉ፤


ስለዚህ በነቢያት እጅ ቆረጥኋቸው፥ በአፌም ቃላት ገደልኋቸው፤ ፍርዴም እንደ ብርሃን ይወጣል።


“ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ላይ ተቀምጠዋል፤


ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ፥ ሲለዩአችሁና ሲነቅፉአችሁ፥ በክፉም ስማችሁን ሲያጠፉ ብፁዓን ናችሁ!


ከምኵራባቸው ያስወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል።


እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች የክርስቶስን ሐዋርያት ለመምሰል ራሳቸውን ቢለዋውጡም፥ ሐሰተኛ ሐዋርያትና አጭበርባሪ ሠራተኞች ናቸው።


ስለ ቅንዓት ብትጠይቁ፥ ቤተ ክርስቲያንን አሳዳጅ ነበርሁ፤ በሕግ ስለሚገኝ ጽድቅ ብትጠይቁ፥ ያለ ነቀፋ ነበርሁ።


የእምነታችንንም ራስና ፍጽምና የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፥ ውርደቱንም ንቆ፥ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos