Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ማሕልየ መሓልይ 2:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እነሆ፥ የውዴ ድምፅ! በተራሮች ላይ ሲዘልል በኮረብቶችም ላይ ሲወረወር ይመጣል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እነሆ፤ የውዴ ድምፅ በተራሮች ላይ እየዘለለ፣ በኰረብቶችም ላይ እየተወረወረ፣ ሲመጣ ይሰማኛል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ውዴ በተራሮችና በኮረብቶች ላይ እየዘለለና እየተወረወረ ሲመጣ ድምፁ ይሰማል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እነሆ፥ የልጅ ወን​ድሜ ቃል በተ​ራ​ሮች ላይ ሲዘ​ልል፥ በኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም ላይ ሲወ​ረ​ወር ይመ​ጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እነሆ፥ የውዴ ቃል! በተራሮች ላይ ሲዘልል በኮረብቶችም ላይ ሲወረወር ይመጣል።

Ver Capítulo Copiar




ማሕልየ መሓልይ 2:8
19 Referencias Cruzadas  

የጌታ ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ ሲገባ፥ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ትመለከት ነበር፤ ንጉሥ ዳዊት በጌታ ፊት ሲዘልና ሲያሸበሽብ ባየችው ጊዜ በልቧ ናቀችው።


ውዴ ሆይ፥ ቀኑ እስኪነፍስ፥ ጥላውም እስኪሸሽ ድረስ ተመለስ፥ በወጣ ገባ ተራራ ላይ ሚዳቋውን ወይም የዋላውን እምቦሳ ምሰል።


የሰሜን ነፋስ ሆይ፥ ተነሥ፥ የደቡብም ነፋስ ና፥ በገነቴ ላይ ንፈስ፥ ሽቱውም ይፍሰስ፥ ውዴ ወደ ገነቱ ይግባ ምርጡንም ፍሬ ይብላ።


እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን ነቅቶአል፥ የውዴ ድምፅ ነው፥ እርሱም ያንኳኳል፥ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ የእኔ እንከን የለሽ፥ ራሴ በጠል፥ ጸጉሬም በሌሊት ነጠብጣብ ርሶአል።


በዚያን ጊዜ በምድረ በዳ ውኃ፥ በበረሀም ምንጭ ይፈልቃልና አንካሳ እንደ ሚዳቋ ይዘላል፤ የድዳም ምላስ ይዘምራል።


ሰማያት ሆይ፥ ጌታ አድርጎታልና ዘምሩ፤ ጌታ ያዕቆብን ተቤዥቶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ ይከበራልና አንተ የምድር ጥልቅ ሆይ፥ ጩኽ፤ እናንተም ተራሮች አንተም ዱር በአንተም ያለ ዛፍ ሁሉ፥ እልል በሉ።


የምሥራች የሚናገር፥ ሰላምንም የሚያወራ፥ የመልካምንም ወሬ የምሥራች የሚናገር፥ መድኃኒትንም የሚያወራ፥ ጽዮንንም፦ አምላክሽ ነግሦአል የሚል ሰው እግሩ በተራሮች ላይ እጅግ ውብ ነው።


ለአንተ እስራኤል መሳቂያ አልነበረምን? ወይስ ስለ እርሱ በተናገርህ ቊጥር ራስህን የምትነቀንቀው በሌቦች መካከል ተገኝቶአልን?።


እነሆ፥ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና፤ በዚያን ቀን ተደሰቱ፤ በደስታም ዝለሉ፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና።


በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ፤ እኔም አውቃቸዋለሁ፤ ይከተሉኝማል፤


ሙሽራይቱ ያለችው እርሱ ሙሽራ ነው፤ ቆሞ የሚሰማው ሚዜው ግን በሙሽራው ድምጽ እጅግ ደስ ይለዋል። እንግዲህ ይህ ደስታዬ ተፈጸመ።


በታላቅ ድምፅ “ቀጥ ብለህ በእግርህ ቁም፤” አለው። ብድግ ብሎም ተንሥቶ ይመላለስ ነበር።


ወደ ላይ ዘሎም ቆመ፤ ይመላለስም ጀመር፤ እየተመላለሰም እየዘለለም እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋር ወደ መቅደስ ገባ።


እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ፤ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos