Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሮሜ 4:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 “ዘርህም እንዲሁ ይሆናል” ተብሎ እንደ ተነገረው፥ ተስፋ በሌለበት የብዙ ሕዝቦች አባት እንደሚሆን በተስፋ አመነ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 “ዘርህም እንዲሁ ይሆናል” ተብሎ ለርሱ በተነገረው መሠረት፣ ምንም ተስፋ በሌለበት፣ አብርሃም በተስፋ አምኖ የብዙ ሕዝብ አባት ሆነ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 አብርሃም ዘርህ እጅግ ይበዛል ተብሎ በተነገረው መሠረት የብዙ ሕዝብ አባት እንደሚሆን ያመነውና ተስፋ ያደረገው ምንም ተስፋ በማይጣልበት ነገር ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 አብ​ር​ሃም “ዘርህ እን​ዲሁ ይሆ​ናል” ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተስፋ እንደ ሰጠው ተስፋ ባል​ነ​በረ ጊዜ የብ​ዙ​ዎች አሕ​ዛብ አባት እን​ደ​ሚ​ሆን አመነ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ዘርህ እንዲሁ ሊሆን ነው እንደ ተባለ፥ ተስፋ ባልሆነው ጊዜ የብዙ አሕዛብ አባት እንዲሆን ተስፋ ይዞ አመነ።

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 4:18
12 Referencias Cruzadas  

የምትዘገይ ተስፋ ልብን ታሳዝናለች፥ የተገኘች ፈቃድ ግን የሕይወት ዛፍ ናት።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ አጥንቶች መላው የእስራኤል ቤት ናቸው፤ እነሆ፦ “አጥንቶቻችን ደርቀዋል ተስፋችንም ጠፍቶአል፤ ፈጽመን ተቆርጠናል” ይላሉ።


ዘካርያስም መልአኩን፦ “እኔ ሽማግሌ ነኝ፤ ሚስቴም በዕድሜዋ ገፍታለችና ይህንን በምን አውቃለሁ?” አለው።


ስለዚህ እናንተ ሰዎች ሆይ! አይዞአችሁ፤ እንደ ተናገረኝ እንዲሁ እንዲሆን እግዚአብሔርን አምናለሁ።


“የብዙ ሕዝቦች አባት አድርጌሃለሁ” ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ የሞተውን ሕያው በሚያደርግ የሌለውንም እንዳለ አድርጎ በሚጠራ ባመነበት አምላክ ፊት ነው።


መቶ ዓመት ሆኖት ሳለ ምውት የሆነውን የራሱን አካልና የሳራ ማኅፀን ምውት መሆን አስቦ በእምነት አልደከመም፤


ተስፋም ቅር አያሰኘንም፤ ምክንያቱም በተሰጠን በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ነው።


በዚህ ተስፋ ድነናል፤ ነገር ግን ተስፋው የሚታይ ከሆነ ተስፋ አይደለም፤ የሚያየውንማ ማን ተስፋ ያደርገዋል?


ይህም ተስፋ እንደ ነፍስ መልሕቅ አለን፤ እርሱም እርግጥና ጽኑ የሆነ ወደ መጋረጃውም ውስጥ የገባ ነው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos