Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሮሜ 2:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 የሞኞች አስተማሪ፥ የሕፃናት መምህር ነኝ ካልህ፥ በሕግም የእውቀትና የእውነት አርአያ ካለህ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በሕጉም ካገኘኸው ዕውቀትና እውነት የተነሣ አላዋቂ ለሆኑት መካሪ፣ ለሕፃናት አስተማሪ ከሆንህ፣

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ያልተማሩትን አሠለጥናለሁ፤ ሕፃናትን አስተምራለሁ” ትላለህ፤ እንዲሁም “በሕግ የዕውቀትና የእውነት ምልአት አለኝ” ትላለህ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሰነ​ፎ​ችን ልባ​ሞች የም​ታ​ደ​ርግ፥ ሕፃ​ና​ትን የም​ታ​ስ​ተ​ምር፥ ጻድ​ቅና የም​ት​ከ​ብ​ር​በ​ትን የኦ​ሪ​ትን ሕግ የም​ታ​ውቅ የም​ት​መ​ስል፥

Ver Capítulo Copiar




ሮሜ 2:20
11 Referencias Cruzadas  

የሃይማኖትን መልክ የያዙ ነገር ግን ኃይሉን የካዱ ሆነው ይገኛሉ፤ እንደነዚህ ካሉት ሰዎች ራቅ።


እግዚአብሔርን እንደሚያውቁ በግልጥ ይናገራሉ ዳሩ ግን በሥራቸው ይክዱታል፤ የሚያጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ ብቁ ያልሆኑ ናቸው።


በክርስቶስ ኢየሱስ ባለ እምነትና ፍቅር ከእኔ የሰማኸውን እውነተኛ ቃላት ምሳሌ አድርገህ ያዝ፤


ወንድሞች ሆይ! እኔም፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም።


አስቀድማችሁ የኃጢአት ባርያዎች የነበራችሁ፥ ነገር ግን ለተሰጣችሁለት የትምህርት ዓይነት ከልባችሁ በመታዘዛችሁ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።


ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ፥ አዲስ እንደ ተወለዱ ሕፃናት ንጹሑን መንፈሳዊ ወተት ተመኙ፤


ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ የጽድቅን ቃል አያውቅም፤


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ “የሰማያትና የምድር ጌታ አባት ሆይ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ።


ለዓይነ ስውሮች መሪ፥ በጨለማ ላሉትም ብርሃን እንደሆንህ በራስህ የምትተማመን ከሆነ፥


ስለዚህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? በጭራሽ! ነገር ግን ሕግን እናጸናለን።


ወንድሞቼ ሆይ! ከእናንተ ብዙዎች አስተማሪዎች አይሁኑ፤ ምክንያቱም አስተማሪዎች የሆንን የባሰ ፍርድ እንደምንቀበል ታውቃላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios