Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 89:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ጽኑ ፍቅሩን ከእርሱ አላርቅም፥ በእውነቴም አልበድልም፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ኪዳኔን አላፈርስም፤ ከአፌ የወጣውንም አላጥፍም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ከእርሱ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አላፈርስም፤ ለእርሱ ከሰጠሁትም የተስፋ ቃል አንዱን እንኳ አላስቀርም።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 89:34
11 Referencias Cruzadas  

ሐሰትን ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ሰው አይደለም፥ ይጸጸትም ዘንድ የሰው ልጅ አይደለም። እርሱ ያለውን አያደርገውምን? የተናገረውንስ አይፈጽመውምን?


መልካም ስጦታ ሁሉ፥ ፍጹምም በረከት ሁሉ፥ እንደ ጥላ መዘዋወር ወይም መለዋወጥ ከሌለበት ከላይ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


እኔ ጌታ አልለወጥምና፤ ስለዚህ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ አልጠፋችሁም።


እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትምና።


ስለ ስምህ ብለህ አትናቀን፥ የክብርህንም ዙፋን አታዋርድ፤ ከእኛ ጋርም ያደረግኸውን ቃል ኪዳንህን አስታውስ እንጂ አታፍርስ።


በዚህ ነገር ሁሉ ግን እኔ ጌታ አምላካቸው ነኝና እነርሱ በጠላቶቻቸው ምድር ሳሉ፥ ፈጽሞ እስካጠፋቸው ድረስ ከእነርሱም ጋር ያለኝን ቃል ኪዳን እስካፈርስ ድረስ አልጥላቸውም አልጸየፋቸውምም።


“ጌታ እንዲህ ይላል፦ ቀንና ሌሊት በተመደበላቸው ጊዜ እንዳይሆኑ የቀን ቃል ኪዳኔንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን ማፍረስ ብትችሉ፥


ከአንተ በፊት ካስወገድሁት ከሳኦል ምሕረቴን እንዳራቅሁ ከእርሱ ግን አላርቅም።


በሰሎሞን ኃጢአት ምክንያት የዳዊትን ትውልዶች እቀጣለሁ፤ ይሁን እንጂ የምቀጣቸው ለዘለዓለም አይደለም።’”


እኔም አባት እሆነዋለሁ፥ እርሱም ልጅ ይሆነኛል፤ ጽኑ ፍቅሬን ከአንተ በፊት ከነበረው ላይ እንደወሰድሁ ከእርሱ ላይ ከቶውንም አልወስድም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios