Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 89:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ኃጢአታቸውን በበትር፥ በደላቸውንም በመቅሠፍት እጐበኛታለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ምሕረቴን ግን ከርሱ አላርቅም፤ ታማኝነቴንም አላጓድልበትም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ነገር ግን ለዳዊት ያለኝ ፍቅር ከቶ አይገታም፤ ለእርሱ የሰጠሁትንም የተስፋ ቃል ከመፈጸም ወደ ኋላ አልልም።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 89:33
13 Referencias Cruzadas  

ከአንተ በፊት ካስወገድሁት ከሳኦል ምሕረቴን እንዳራቅሁ ከእርሱ ግን አላርቅም።


ይሄውም እግዚአብሔር ሊዋሽ በማይቻል በሁለት በማይለወጥ ነገር፥ በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት እንዲሆንልን ነው።


የእስራኤል ክብር የሆነው እርሱ አይዋሽም፤ አይጸጸትምም፤ እርሱ ይጸጸት ዘንድ ሰው አይደለም።”


ይሁን እንጂ ስሜ እንዲጠራባት በመረጥኳት በኢየሩሳሌም አገልጋዬ ዳዊት በፊቴ አንድ ዘር ይኖረው ዘንድ ለልጁ አንድ ነገድ እሰጠዋለሁ።


ለአገልጋዬ ለዳዊትና ከሌላው የእስራኤል ምድር የራሴ ርስት እንድትሆን ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል ለሰሎሞን አንድ ነገድ አስቀርቼለታለሁ።


ከልጅህም ቢሆን መንግሥቱን በሙሉ አልወስድበትም፤ ለአገልጋዬ ለዳዊትና ለራሴ ርስት እንድትሆን ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል አንድ ነገድ እተውለታለሁ።”


ለስሜ ቤት የሚሠራ እርሱ ነው፤ እኔም የመንግሥቱን ዙፋን ለዘለዓለም አጸናለሁ።


ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሩ ሥር እስከሚያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋልና።


አንተ ግን ናቅኸው ጣልኸውም፥ በቀባኸውም ላይ በቁጣ ተነሣህ።


አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል። በደል በሚፈጽምበትም ጊዜ ሰዎች በሚቀጡበት በትር እቀጣዋለሁ፤ የሰው ልጆችም በዐለንጋ እንደሚገረፉ እገርፈዋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios