22 እጄም ትረዳዋለች፥ ክንዴም ታጸናዋለች።
22 በጠላት አይበለጥም፤ ክፉ ሰውም አይበግረውም።
22 ጠላት አይረታውም፤ ክፉም ሰው አያዋርደውም።
የራሱ የሆነ መኖሪያ እንዲኖረውና ከእንግዲህ ወዲያ እንዳይናወጥ፥ ለሕዝቤ ለእስራኤል ቦታ እሰጠዋለሁ፤ አጸናዋለሁም። ከእንግዲህ ወዲህ ክፉ ሕዝብ አይጨቁነውም፤ ከዚህ በፊት እንደ ሆነው፥
ለሕዝቤም ለእስራኤል ስፍራን እሰጠዋለሁ፥ በዚያም እተክለዋለሁ፥ በስፍራውም ይቀመጣል፥ ከዚያም በኋላ አይናወጥም፤ ከእንግዲህም ወዲያ እንደ ቀድሞው ዘመን ዓመፀኞች አያስጨንቁትም፤
ከእነርሱ ጋር በዓለም ሳለሁ የሰጠኸኝን እኔ በስምህ እጠብቃቸው ነበር፤ ጠበቅኋቸውም፤ የመጽሐፉም ቃል እንዲፈጸም ከጥፋት ልጅ በቀር ከእነርሱ ማንም አልጠፋም።
ማንም ሰው በማናቸውም መንገድ አያታልላችሁ፤ ከሐዲው አስቀድሞ ሳይመጣ የዓመፅም ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ ያ ቀን አይመጣምና።