Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 81:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ሕዝቤ ሆይ፥ ስማኝ እነግርሃለሁም፥ እስራኤል ሆይ፥ ምነው በሰማኸኝ!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በአንተ ዘንድ ባዕድ አምላክ አይኑር፤ ለሌላም አምላክ አትስገድ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ባዕድ አምላክ አይኑርህ፤ እርሱንም አታምልክ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 81:9
12 Referencias Cruzadas  

ተናግሬአለሁ፥ አድኛለሁ፥ አሳይቻለሁ፥ በእናንተም ዘንድ ባዕድ አምላክ አልነበረም፤ ስለዚህ እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ፥ ይላል ጌታ።


ጌታ ብቻውን መራው፥ ከእርሱም ጋር ባዕድ አምላክ አልነበረም።”


በዙሪያህ ያሉት አሕዛብ የሚያመልኩአቸውን ሌሎችን አማልክት አትከተል።


ይሁዳ አታልሎአል፥ በእስራኤልና በኢየሩሳሌም ውስጥ ርኩሰት ሠርቷል፤ ይሁዳ ጌታ የወደደውን መቅደስ አርክሶአል፥ የባዕድንም አምላክ ልጅ አግብቶአል።


በክፉ ስፍራ አዋርደኸናልና፥ በሞት ጥላም ሰውረኸናልና።


እርሱም፦ “አንተ የጌታ አምላክህን ቃል ብትሰማ፥ በፊቱም ትክክል የሆነውን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላመጣብህም፤ ፈዋሽህ እኔ ጌታ ነኝና” አለ።


ሚክያስም ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ ጌታ የሚለውን ስማ! ጌታ በሰማይ ባለው ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ፥ መላእክቱም ሁሉ በቀኝና በግራው ቆመው አየሁ፤


ሕዝቤ፥ ስማኝ፥ ልንገርህ፥ እስራኤልም፥ ስማኝ፥ ልመስክርብህ፥ አምላክስ እኔ አምላክህ ነኝ።


አድምጡ ድምፄንም ስሙ፤ ልብ አድርጉ ንግግሬንም ስሙ።


እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ! እውነትና ጽኑ ፍቅር አምላክንም ማወቅ በምድሪቱ ስለ ሌለ ጌታ በምድሪቱ ላይ ከሚኖሩ ጋር ሙግት አለውና የጌታን ቃል ስሙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios