Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 78:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ተስፋቸውን በእግዚአብሔር እንዲያደርጉ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ እንዳይረሱ፥ ትእዛዙንም እንዲጠብቁ፥

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እነርሱም በእግዚአብሔር ይታመናሉ፤ የእርሱንም ሥራ አይረሱም፤ ትእዛዞቹንም ይጠብቃሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 በዚህ ዐይነት እነርሱም በእግዚአብሔር ላይ ይታመናሉ፤ ትእዛዞቹንም ዘወትር ይፈጽማሉ እንጂ ያደረገውን ሁሉ አይረሱም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ያዕ​ቆ​ብን በል​ተ​ው​ታ​ልና፥ ስፍ​ራ​ው​ንም ባድማ አድ​ር​ገ​ዋ​ልና።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 78:7
26 Referencias Cruzadas  

እኔንም ለመፍራት ሁልጊዜም ትእዛዜን ሁሉ ለመጠበቅ፥ እንዲህ ያለ ልብ ምነው ሁልግዜ በኖራቸው! ለእነርሱ ለልጆቻቸውም ለዘለዓለም መልካም በሆነላቸው ነበር!


የእግዚአብሔርን ትእዛዛትና የኢየሱስን እምነት የሚጠብቁት ቅዱሳን እዚህ ላይ ነው ጽናታቸው የሚፈለገው።


ትእዛዛቱን እንድንጠብቅ፥ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።


“ብቻ አስተውል፥ ነፍስህንም በትጋት ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይለይ፥ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አሳውቃቸው።


ነፍሴ ሆይ፥ ጌታን ባርኪ፥ ውለታውንም ከቶ አትርሺ፥


በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፥ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።


አዲስ ዝማሬን ለአምላካችን ምስጋና በአፌ ጨመረ፥ ብዙዎች ያያሉ ይፈሩማል፥ በጌታም ይታመናሉ።


“ዛሬ እኔ አንተን የማዘውን ትእዛዞቹንና ፍርዱን ሥርዓቱንም ባለመጠበቅ፥ ጌታ አምላክህን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ።


ጌታ አምላክህ ሊያስጨንቅህ፥ ትእዛዙን ትጠብቅ ወይም አትጠብቅ እንደሆነ፥ በልብህ ያለውን ያውቅ ዘንድ ሊፈትንህ፥ በእነዚህ በአርባ ዓመታት በምድረ በዳ የመራህን መንገድ ሁሉ አስታውስ።


እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ፥ ከሞት ባስነሣው ክብርንም በሰጠው፥ በእግዚአብሔር በእርሱ ትተማመናላችሁ።


አመሰገነ ቆርሶም “እንካችሁ ብሉ፤ ይህ ስለ እናንተ የሚሆን ሥጋዬ ነው፤ ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት፤” አለ።


የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ ተስፋውም በጌታ በአምላኩ የሆነ ሰው ምስጉን ነው፥


አገልጋዮቹ የአብርሃም ዘር፥ ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፥ የሠራውን ድንቅ ሥር አስቡ፥ ተአምራቱን የተናገረውንም ፍርድ።


ከከፍታ ያናውጡት ዘንድ መከሩ፥ ሐሰትንም ይወድዳሉ፥ በአፋቸው ይባርካሉ፥ በልባቸውም ይረግማሉ።


በዚያን ጊዜ ከግብጽ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን ጌታ እንዳትረሳ ተጠንቀቅ።


አንተም ልጅህን እንዲህ ትለዋለህ፥ ‘በግብጽ የፈርዖን ባርያዎች ነበርን፤ ጌታም በጽኑ እጅ ከግብጽ አወጣን፥


እርሱም እንዳዘዘን በጌታ አምላካችን ፊት እነዚህን ትእዛዛት ሁሉ ለመፈጸም ብንጠነቀቅ ለእኛ ጽድቅ ይሆንልናል።’


ሕጉን ይጠብቁ ዘንድ፥ ሥርዓቱንም ይፈልጉ ዘንድ። ሃሌ ሉያ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios