23 ስለ አንተ ሁልጊዜ ተገድለናል፥ እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል።
23 ጌታ ሆይ፤ ንቃ! ለምንስ ትተኛለህ? ተነሥ፤ ለዘላለምም አትጣለን።
23 ጌታ ሆይ! ንቃ! ስለምንስ ታንቀላፋለህ? ተነሥ! ለዘለዓለም አትተወን!
ጌታ ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፥ በወይን ኃይል እንደተበረታታ ጀግና፥
ጠላት ነፍሴን ያሳድዳት ያግኛትም፥ ሕይወቴንም በምድር ላይ ይርገጣት፥ ክብሬንም በትቢያ ላይ ያዋርዳት።
የአሳፍ ትምህርት። አቤቱ፥ ስለምን ለሁልጊዜ ጣልኸኝ? በማሰማርያህ በጎች ላይስ ቁጣህ ስለምን ጨሰ?
አምላኬ ጌታዬም፥ ትፈርድልኝ ዘንድ ተነሥ፥ አቤቱ፥ ፍርዴን አድምጥ።
እርሱም በስተኋላዋ ትራስ ተንተርሶ ተኝቶ ነበር፤ ቀስቅሰውትም “መምህር ሆይ! ስንጠፋ አይገድህምን?” አሉት።
የጌታ ክንድ ሆይ! ተነሥ፥ ተነሥ፥ ኃይልንም ልበስ፤ በቀድሞው ወራትና በጥንቱ ዘመን በነበረው ትውልድ እንደ ሆነው ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?
አቤቱ፥ እኔ ግን ወደ አንተ ጮኽሁ፥ በጥዋት ጸሎቴ ወደ ፊትህ ትደርሳለች።
በሌሊት ከልቤ ጋር ተጫወትሁ፥ ነፍሴንም አነቃቃኋት።
ሁልጊዜ በእግዚአብሔር እንከብራለን፥ ስምህንም ለዘለዓለም እናመሰግናለን።
ምላሳችንን እናበረታለን፥ ከንፈራችን የእኛ ነው፥ ጌታችን ማን ነው? የሚሉትን።