Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 37:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 የጻድቃን መድኃኒታቸው በጌታ ዘንድ ነው፥ በመከራቸውም ጊዜ መጠጊያቸው እርሱ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 የጻድቃን ድነት ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤ በመከራ ጊዜም መጠጊያቸው እርሱ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 የጻድቃን መዳን የሚመጣው ከእግዚአብሔር ነው፤ በችግር ጊዜ መጠጊያቸው እርሱ ነው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 37:39
20 Referencias Cruzadas  

እርሱም ዓለምን በጽድቅ ይፈርዳታል፥ አሕዛብንም በቅንነት ይዳኛቸዋል።


ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፥ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።


ዳሩ ግን የስብከቱ ሥራ በእኔ እንዲፈጸም አሕዛብም ሁሉ እንዲሰሙት፥ ከእኔ ጎን ጌታ ቆመ አበረታኝም፤ ከአንበሳም አፍ ዳንሁ።


እነሆ፤ ጌታ መዳኛዬ ነው፤ እታመናለሁ፤ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ የመዳኔ ምክንያትም ሆኖአል።”


ተነሥ፥ አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፥ አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተሃልና፥ የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረሃልና።


ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ምሥጢር፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር።


ጸጋው በእምነት አድኗችኋልና፤ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ የመጣም አይደለም።


እንደ ክብሩ ኃያልነት በሁሉ ኃይል እንድትበረቱና ሁሉንም ነገር በትዕግሥት በጽኑ ለመወጣት እንድትዘጋጁ እንዲሁም ደስ በመሰኘት


ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ ምሕረታቸውን ትተዋል።


አቤቱ ጌታ ሆይ፥ ማረን፤ አንተን እንጠባበቃለን፤ በየእለቱ ክንዳችን፥ በመከራም ጊዜ መድኅኒት ሁነን።


በሚዋጉበትም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኸዋልና፥ በእርሱም ታምነዋልና ተለመናቸው፤ እነርሱንም ረዳቸው፥ አጋራውያንና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም ሁሉ በእጃቸው ተላልፈው ተሰጡ።


እንዲሁም ጌታ ሕዝቅያስንና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ከአሦር ንጉሥ ከሰናክሬም እጅ ከጠላቶቻቸውም ሁሉ እጅ አዳናቸው፤ በዙሪያቸውም ካለው ሁሉ አሳረፋቸው።


ጌታ ለተጨቆኑ መጠጊያ ይሁናቸው፥ በመከራም ጊዜ መሸሸጊያ ይሁንላቸው።


ጌታ ኃይሌና ጋሻዬ ነው፥ ልቤ በእርሱ ታመነ እኔም ተረዳሁ፥ ልቤም ደስ ይለዋል፥ ፈቅጄም አመሰግነዋለሁ።


የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥ ጌታ ግን ከሁሉ ያድናቸዋል።


አምላካችን መጠጊያችንና ኃይላችን፥ ባገኘን በታላቅ መከራም ረዳታችን ነው።


ነፍሴ በጸጥታ እግዚአብሔርን ትጠብቅ የለምን? መድኃኒቴ ከእርሱ ዘንድ ናትና።


ጻድቅ ከጭንቀት ይድናል፥ ክፉ ግን የእርሱን ቦታ ይወስዳል።


ለዚህም ሕዝብ የተመሸገ የናስ ቅጥር አደርግሃለሁ፤ ይዋጉሃል እኔ ግን ላድንህና ልታደግህ ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም፥ ይላል ጌታ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios