Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 31:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አቤቱ በአንተ ታመንሁ፥ ለዘለዓለም አልፈር፥ በጽድቅህም አድነኝ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ ፈጥነህ አድነኝ፤ መጠጊያ ዐለት ሁነኝ፤ ታድነኝም ዘንድ ምሽግ ሁነኝ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ጌታ ሆይ! አድምጠኝ፤ ፈጥነህም በመምጣት አድነኝ፤ መጠጊያ አለትና ጠንካራ ምሽግ ሆነህ አድነኝ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በደ​ሉን የማ​ይ​ቈ​ጥ​ር​በት በል​ቡም ሽን​ገላ የሌ​ለ​በት ሰው ብፁዕ ነው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 31:2
24 Referencias Cruzadas  

አቤቱ፥ ጸሎቴን ስማኝ፥ ጩኸቴም ወደ አንተ ይድረስ።


የዳዊት ጸሎት አቤቱ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል አድምጠኝም፥ ደሃና ችግረኛ ነኝና።


አቤቱ፥ ድምፄን ስማ፥ ጆሮህ የልመናዬን ቃል ያድምጥ።


ጠላቶቻችን እንኳ እንደሚስማሙበት፥ ዓለታቸው እንደ እኛ ዓለት አይደለም።


እግዚአብሔርን ያየው ማንም የለም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል፥ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል።


ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል፤ እኔም በእርሱ እኖራለሁ።


ፈጥኖ ይፈርድላቸዋል እላችኋለሁ። ነገር ግን የሰው ልጅ በመጣ ጊዜ በምድር እምነትን ያገኝ ይሆንን?”


እርሱ ከፍ ባለ ሥፍራ ይቀመጣል፤ ጠንካራ አምባ መጠጊያው ይሆናል፤ እንጀራም ይሰጠዋል፥ ውኃውም የማታቋርጥ ትሆናለች።


ጆሮህን አዘንብለህ የጠቢባንን ቃላት ስማ፥ ልብህንም ወደ እውቀቴ አድርግ፥


አቤቱ፥ ፈጥነህ ስማኝ፥ መንፈሴ ዛለ፥ ፊትህን ከኔ አትሰውር፥ ወደ ጉድጓድም እንደሚወርዱ እንዳልሆን።


ጌታ መጠጊያ ሆነኝ፥ አምላኬ የመጠለያዬ ዓለት ነው።


ጌታን፥ “አንተ ተስፋዬ ነህ” ብለህ፥ ልዑልን መጠጊያህ አድርገሃልና።


የእግዚአብሔር ሰው የሙሴ ጸሎት። አቤቱ፥ አንተ ለትውልድ ሁሉ መጠጊያ ሆንህልን።


የአሳፍ መዝሙር። አቤቱ፥ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ፥ ቅዱሱን መቅደስህንም አረከሱ፥ ኢየሩሳሌምንም አፈራረሱአት።


አቤቱ፥ ቸርነትህ መልካም ናትና ስማኝ። እንደ ርኅራኄህም ብዛት ወደ እኔ ተመልከት፥


እርሱ ዓለቴም መድኃኒቴም ነውና፥ እርሱ መጠጊያዬ ነው፥ አልታወክም።


አቤቱ፥ የሚፈልጉህ ሁሉ በአንተ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ፥ ሁልጊዜ ማዳንህን የሚወድዱ ዘወትር፦ ጌታ ታላቅ ይሁን ይበሉ።


ስለምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኃጢአቴንስ ስለምን አታስወግድልኝም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፥ ትፈልገኛለህ፥ እኔ ግን የለሁም።”


አምላኬ የምደገፍበት፥ ዐለቴ፥ ጋሻዬና የመዳኔ ቀንድ ነው። እርሱም ጠንካራ ምሽጌ፥ መጠጊያና አዳኜ ነው፤ አንተ ከጨካኞች ታድነኛለህ።


አቤቱ አምላኬ፥ በአንተ ታመንሁ፥ ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝና አውጣኝ፥


አምላኬ፥ በአንተ ታመንሁ፥ አልፈር፥ ጠላቶቼ በእኔ አይሣቁብኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios