62 ስለ ጽድቅህ ፍርድ፥ በእኩለ ሌሊት አመሰግንህ ዘንድ እነሣለሁ።
62 ስለ ጻድቅ ሥርዐትህ፣ በእኩለ ሌሊት ላመሰግንህ እነሣለሁ።
62 ስለ ትክክለኛ ፍርድህ አንተን ለማመስገን በእኩለ ሌሊት እነሣለሁ።
በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፤ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር
ማለዳም ገና ጎሕ ሳይቀድ፥ ኢየሱስ ተነሥቶ ከቤት ወጣ፤ ወደ አንድ ገለልተኛ ስፍራም ሄዶ ይጸልይ ጀመር።
በፏፏቴህ ድምፅ ቀላይ ቀላይን ትጠራታለች፥ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፈ።
ስለ ጽድቅህ ፍርድ ሰባት ጊዜ በቀን አመሰግንሃለሁ።
አቤቱ፥ ትክክለኛ ፍርድህን ስማር በቅን ልብ አመሰግንሃለሁ።
ስለዚህ ሕጉ ቅዱስ ነው፤ ትእዛዙም ቅዱስ፥ ትክክለኛና መልካም ነው።
ማለዳ ጮኽሁ፥ ቃልህንም ተስፋ አድርጌአለሁ።
አቤቱ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፥ ፍርድህም ቅን ነው።
አቤቱ፥ ፍርድህ ጽድቅ እንደ ሆነች፥ በእውነትህም እንዳስቸገርኸኝ አወቅሁ።
የጌታ ሥርዓት ቅን ነው፥ ልብንም ደስ ያሰኛል፥ የጌታ ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ ዓይንንም ያበራል።
በዓይናችሁ ፊት ዛሬ እንዳኖርኩት እንደዚህ ሕግ ሁሉ ጽድቅ የሆነች ሥርዓትና ሕግጋት ያለው ታላቅ ሕዝብስ የት ይገኛል?
የጽድቅህን ፍርድ እጠብቅ ዘንድ ማልሁ፥ አጸናሁም።