14 በሕዝቡ ሁሉ ፊት፥ እነሆ ስእለቴን ለጌታ እፈጽማለሁ።
14 በሕዝቡ ሁሉ ፊት፣ ስእለቴን ለእግዚአብሔር እፈጽማለሁ።
14 በሕዝብ ጉባኤ ፊት ተገኝቼ ለእግዚአብሔር የተሳልኩትን አቀርባለሁ።
የችግረኛን ችግር አልናቀምና፥ ቸልም አላለምና፥ ፊቱንም አልሰወረምና፥ ነገር ግን ወደ እርሱ በጮኸ ጊዜ ሰማው።
ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ ምሕረታቸውን ትተዋል።
በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለጌታ እፈጽማለሁ፥
ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ፥
“ደግሞም ለቀደሙት ‘በውሸት አትማል ነገር ግን የማልኸውንም ለጌታ ስጥ’ እንደተባለ ሰምታችኋል።
በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም፥ ሰው ምን ያደርገኛል?
ሰዎቹም ጌታን እጅግ ፈሩ፥ ለጌታም መሥዋዕትን ሠዉ፥ ስእለትንም ተሳሉ።
በታላቅ ጉባኤ ምስጋናዬ ከአንተ ዘንድ ነው። እርሱን በሚፈሩት ፊት ስእለቴን እሰጣለሁ።
አቤቱ፥ በጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል፥ ለአንተም ስእለት ይቀርባል።