ዘኍል 31:50 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)50 ሰውም ሁሉ ካገኘው ከወርቅ ዕቃ፥ ከእግር አልቦም፥ ከአምባርም፥ ከቀለበትም፥ ከጉትቻም፥ ከወርቁም ጌጣጌጥ ለነፍሳችን በጌታ ፊት እንዲያስተሰርይልን ለጌታ መባ አምጥተናል።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም50 ስለዚህ እያንዳንዳችን ያገኘነውን የወርቅ ጌጣጌጥ፣ የእግር ዐልቦዎች፣ የእጅ አንባሮች፣ የጣት ቀለበቶች፣ የጆሮ ጕትቻዎችና የዐንገት ሐብሎች በእግዚአብሔር ፊት ማስተስረያ እንዲሆነን መባ አድርገን ለእግዚአብሔር አምጥተናል።” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም50 ስለዚህ እያንዳንዳችን ያገኘነውን የወርቅ ጌጣጌጥ ማለትም የእግር አልቦውን፥ የእጅ አንባሩን፥ የጣት ቀለበቱን፥ የጆሮ ጒትቻውንና የአንገት ድሪውን ሁሉ ለኃጢአታችን ማስተስረያ ለእግዚአብሔር ቊርባን ይሆን ዘንድ ይዘን መጥተናል።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)50 ሰውም ሁሉ ከአገኘው ከወርቅ ዕቃ፥ ከእግር አልቦም፥ ከአምባርም፥ ከቀለበትም ከጕትቻም፥ ከድሪውም ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ታስተሰርዩልን ዘንድ ለእግዚአብሔር መባ አምጥተናል” አሉት። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)50 ሰውም ሁሉ ካገኘው ከወርቅ ዕቃ፥ ከእግር አልቦም፥ ከአምባርም፥ ከቀለበትም፥ ከጉትቻም፥ ከድሪውም ለነፍሳችን በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይልን ዘንድ ለእግዚአብሔር መባ አምጥተናል አሉት። Ver Capítulo |