ዘኍል 27:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 የሰለጰዓድም ሴቶች ልጆች ቀረቡ፤ እርሱም ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ወገኖች፥ የምናሴ ልጅ የማኪር ልጅ የገለዓድ ልጅ የኦፌር ልጅ ነበር፤ የእነዚህም ሴቶች ልጆች ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የገለዓድ ልጅ፣ የአፌር ልጅ፣ የሰለጰዓድ ሴት ልጆች ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ጐሣዎች ነበሩ፤ ስማቸውም ማህለህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካና ቲርጻ ይባላል። እነርሱም፣ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 የሔፌር፥ የገለዓድ፥ የማኪር፥ የምናሴ፥ የዮሴፍ ልጅ የሆነው ጸሎፍሐድ፥ ማሕላ፥ ኖዓ፥ ሖግላ፥ ሚልካ እና ቲርጻ ተብለው የሚጠሩ ሴቶች ልጆች ነበሩት። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ወገን ፥ የምናሴ ልጅ፥ የማኪር ልጅ፥ የገለአድ ልጅ፥ የኦፌር ልጅ፥ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች መጡ፤ የእነዚህም ሴቶች ልጆች ስሞች መሐላ፥ ኑኃ፥ ሄግላ፥ ሚልካ፥ ቴርሳ ነበሩ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ከዮሴፍ ልጅ ከምናሴ ወገኖች፥ የምናሴ ልጅ የማኪር ልጅ የገለዓድ ልጅ የኦፌር ልጅ የሰለጰዓድ ሴቶች ልጆች ቀረቡ፤ የእነዚህም ሴቶች ልጆች ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ። Ver Capítulo |