ዘኍል 15:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)38 “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ እነርሱም ትውልዶቻቸውም በልብሳቸው ጫፍ ዘርፍ እንዲያደርጉ፥ በዘርፉም ጫፍ ሁሉ ላይ ሰማያዊ ፈትል እንዲያኖሩበት እዘዛቸው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም38 “እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘በሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ በየልብሳችሁ ጫፍ ላይ ዘርፍ አድርጉ፤ እያንዳንዱም ዘርፍ ሰማያዊ ጥለት ይኑረው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም38 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘በልብሶቻችሁ ጫፍ ላይ ሁሉ ዘርፍ አብጁ፤ እያንዳንዱም ዘርፍ ከሰማያዊ ፈትል የተሠራ ጥለት ይኑረው፤ ይህንንም ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ አድርጉ፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)38 “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፦ እነርሱም በትውልዳቸው ሁሉ በልብሳቸው ጫፍ ዘርፍ ያደርጉ ዘንድ፥ በዘርፉም ሁሉ ላይ ሰማያዊ ፈትል ያደርጉ ዘንድ እዘዛቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)38 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ በላቸው፦ እነርሱም ትውልዶቻቸውም በልብሳቸው ጫፍ ዘርፍ ያደርጉ ዘንድ፥ በዘርፉም ሁሉ ላይ ሰማያዊ ፈትል ያደርጉ ዘንድ እዘዛቸው። Ver Capítulo |