ዘኍል 10:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ሁለተኛውንም የማስጠንቀቂያ መለከት ከፍ ባለ ድምፅ ስትነፉ በደቡብ በኩል የሰፈሩት ይጓዛሉ፤ የማስጠንቀቅያውን መለከት እንዲጓዙ ለመቀስቀስ ይነፋሉ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 መለከቱ ከፍ ባለ ድምፅ ለሁለተኛ ጊዜ ሲነፋ በስተ ደቡብ የሰፈሩት ነገዶች ጕዞ ይጀምሩ፤ ከፍ ያለው ድምፅ ጕዞ ለመጀመር ምልክት ይሆናል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ለሁለተኛ ጊዜ የማስጠንቀቂያውን ድምፅ ስታሰማ በስተደቡብ የሰፈሩት ሰፋሪዎች ጒዞ ይጀምሩ፤ በዚህም ዐይነት የማስጠንቀቂያ የመለከት ድምፅ የሚነፋው፥ ሰፈር ለቆ ጒዞ በሚጀመርበት ጊዜ ይሆናል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ሁለተኛውንም በምልክቱ ስትነፉ በአዜብ በኩል የሰፈሩት ይጓዙ፤ ሦስተኛውንም በምልክቱ በነፋችሁ ጊዜ በባሕር በኩል የሰፈሩት ይጓዙ፤ አራተኛውንም በምልክቱ በነፋችሁ ጊዜ በመስዕ በኩል የሰፈሩት ሠራዊት ይጓዙ፤ ለማስጓዝ በምልክት ትነፉታላችሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ሁለተኛውንም ከፍ ባለ ድምፅ ስትነፉ በደቡብ በኩል የሰፈሩት ይጓዙ፤ ለማስጓዝ መለከትን ይነፋሉ። Ver Capítulo |