Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ነህምያ 4:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ከዚያን ቀን ጀምሮ እኩሌቶቹ ጎልማሶች ሥራ ሲሠሩ፥ እኩሌቶቹ ጋሻ፥ ጦር፥ ቀስትና ጥሩር ይይዙ ነበር፤ ሹማምቱም ከይሁዳ ቤት ሁሉ በኋላ ይቆሙ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በዚህ ጊዜ የይሁዳ ሕዝብ፣ “የሠራተኞቹ ጕልበት እየደከመ ነው፤ ከፍርስራሹም ብዛት የተነሣ ቅጥሩን መልሰን ለመሥራት አንችልም” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በዚህ ጊዜ የይሁዳ ሰዎች “የሸክም ሥራ እያደከመን ሄደ፤ ገና መነሣት ያለበት ፍርስራሽ ብዙ ነው፤ ቅጽሩን እንሠራ ዘንድ አንችልም” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ይሁ​ዳም፥ “የተ​ሸ​ካ​ሚ​ዎች ኀይል ደከመ፤ ፍር​ስ​ራ​ሹም ብዙ ነው፤ ቅጥ​ሩ​ንም እን​ሠራ ዘንድ አን​ች​ልም” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ይሁዳም፦ የተሸካሚዎች ኃይል ደከመ፥ ፍርስራሹም ብዙ ነው፥ ቅጥሩንም እንሠራ ዘንድ አንችልም አሉ።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 4:10
10 Referencias Cruzadas  

የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ፦ ዘመኑ አልደረሰም፥ የጌታ ቤት የሚሠራበት ዘመን አልደረሰም ይላል።”


የሰው ልጅ ሆይ፥ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በጢሮስ ላይ ሠራዊቱን ጽኑ ሥራ አሠራ፤ ራስ ሁሉ ተመልጧል፥ ትከሻም ሁሉ ተልጦአል፥ ሆኖም በእርሷ ላይ ለሰሩት ሥራ እርሱም ሆነ ሠራዊቱ ከጢሮስ ደመወዝ አልተቀበሉም።


ከእነርሱም የሚሸከሙትን ሰባ ሺህ፥ በተራሮችም ላይ የሚጠርቡትን ሰማንያ ሺህ፥ የሕዝቡንም ሥራ ለሚቆጣጠር የተሾሙትን ሦስት ሺህ ስድስት መቶ ሰዎችን ሾመ።


ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ ሄደው ምድሪቱን ባዩ ጊዜ፥ ጌታ ወደ ሰጣቸው ምድር እንዳይገቡ የእስራኤልን ልጆች ልብ አደከሙ።


ከእርሱ ጋር ወጥተው የነበሩት ሰዎች ግን፦ “ከእኛ ይልቅ እነርሱ ብርቱ ናቸውና በዚህ ሕዝብ ላይ መውጣት አንችልም” አሉ።


በተሸካሚዎችና ልዩ ልዩ ሥራ በሚሠሩ ላይ ተሾመው ነበር፤ ጸሐፊዎቹና አለቆቹም የደጁም ጠባቂዎች ከሌዋውያን ወገን ነበሩ።


መጥተው ኢየሩሳሌምን ሊወጉና ሊሸብሩ ሁሉም በአንድነት አሴሩ።


እንዲህም ሆነ፥ ጠላቶቻችን በእኛ ዘንድ እንደታወቀ፥ እግዚአብሔርም ምክራቸውን ከንቱ እንዳደረገው በሰሙ ጊዜ፥ እኛ ሁላችንም ወደ ቅጥሩ፥ እያንዳንዳችን ወደ ሥራችን ተመለስን።


ቅጥሩን የሚሠሩትና ተሸካሚዎቹ በአንድ እጃቸው ይሠሩ፥ በአንድ እጃቸው ደግሞ የጦር መሣሪያ ይይዙ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios