ነህምያ 2:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 እንዲህም ሆነ በንጉሡ አርታሕሻስት በሀያኛው ዓመት በኒሳን ወር፥ የወይን ጠጅ በፊቱ ነበረ፥ የወይን ጠጁን አንሥቼ ለንጉሡ ሰጠሁት። ከዚህ ቀደም በፊቱ አዝኜ አላውቅም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 በንጉሡ በአርጤክስስ ዘመነ መንግሥት በሃያኛው ዓመት ኒሳን ተብሎ በሚጠራው ወር የወይን ጠጅ በመጣለት ጊዜ፣ የወይን ጠጁን አንሥቼ ለንጉሡ ሰጠሁት። ቀድሞ በፊቱ ዐዝኜ አላውቅም ነበር፤ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 አርጤክስስ በነገሠ በሃያኛው ዓመት ኒሳን ተብሎ በሚጠራው ወር ከዕለታት በአንዱ ቀን ለንጉሠ ነገሥቱ የወይን ጠጅ አቀረብኩለት፤ ከዚያች ቀን በቀር ከዚህ ቀደም በፊቴ ላይ ምንም ዐይነት የሐዘን ምልክት አይቶብኝ አያውቅም ነበር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 በንጉሡ በአርተሰስታ በሃያኛው ዓመተ መንግሥት በኔሳን ወር የወይን ጠጅ በፊቱ ነበር፤ ጠጁንም አንሥቼ ለንጉሡ ሰጠሁት። በፊቱም ሌላ ሰው አልነበረም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 በንጉሡ በአርጤክስስ በሀያኛው ዓመት በኒሳን ወር የወይን ጠጅ በፊቱ በነበረ ጊዜ ጠጁን አንሥቼ ለንጉሡ ሰጠሁት። ቀድሞ ግን በፊቱ ያለ ኃዘን እኖር ነበር። Ver Capítulo |