Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማቴዎስ 18:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 “እንደዚህ ሕፃን ያለውን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ማንም እንደዚህ ያለውን ሕፃን በስሜ የሚቀበል እኔን ይቀበላል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እንደዚህ ያለውን ሕፃን በስሜ የሚቀበል እኔን ይቀበላል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 “እንደዚህም ያለውን አንድ ሕፃን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እንደዚህም ያለውን አንድ ሕፃን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤

Ver Capítulo Copiar




ማቴዎስ 18:5
12 Referencias Cruzadas  

ንጉሡም እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ለሚያንሱት ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ያደረጋችሁት ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው።’


በሥጋዬ ፈተና የሆነባችሁን ነገር አልናቃችሁትም፥ አልተጸየፋችሁትምም፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ፥ እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ ተቀበላችሁኝ።


እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ እኔ የምልከውን ማንኛውንም ሰው የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።”


“ከእነዚህ ሕፃናት አንዱን በስሜ የሚቀበል ሁሉ እኔን ይቀበላል፤ እኔንም የሚቀበለኝ ሁሉ የሚቀበለው እኔን ሳይሆን የላከኝን ነው” አላቸው።


“ማንም ይህን ሕፃን በስሜ የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤ የሚቀበለኝም ሁሉ የላከኝን ይቀበላል፤ በእናንተ መካከል ከሁላችሁ የሚያንስ እርሱ ታላቅ ነውና፤” አላቸው።


እውነት እላችኋለሁ፥ የክርስቶስ በመሆናችሁ በስሜ አንድ ኩባያ ውሃ የሚሰጣችሁ ሁሉ ዋጋውን አያጣም።”


ያንጊዜ እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል ‘እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ለሚያንሱት ከእነዚህ ለአንዱ ያላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ እንዳላደረጋችሁት ነው።’


የሚጠይቅ ሁሉ ይቀበላልና፤ የሚፈልግም ያገኛል፤ የሚያንኳኳ ይከፈትለታል።


እንደዚህ ሕፃን ትሑት የሆነ ሁሉ፥ በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጠው እርሱ ነው።


በእኔ ከሚያምኑ ከእነዚህ ታናናሾች አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ፥ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር ቢሰጥም ይሻለዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios