Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ማርቆስ 11:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እውነት እላችኋለሁ፤ ማንም ይህን ተራራ፥ “ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር” ቢለውና ይህንንም በልቡ ሳይጠራጠር ቢያምን ይሆንለታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እውነት እላችኋለሁ፤ ማንም ይህን ተራራ፣ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር’ ቢለውና ይህንም በልቡ ሳይጠራጠር ቢያምን ይሆንለታል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 በእውነት እላችኋለሁ፤ ማንም ሰው በልቡ ሳይጠራጠር የሚፈልገው ነገር እንደሚፈጸምለት አምኖ ይህን ተራራ ‘ከዚህ ተነሥተህ ወደ ባሕር ተወርወር፤’ ቢል ይሆንለታል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እውነት እላችኋለሁ፤ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር፤’ ቢል ይሆንለታል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እውነት እላችኋለሁ፥ ማንም ያለው ነገር እንዲደረግለት ቢያምን በልቡ ሳይጠራጠር፥ ይህን ተራራ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ቢል ይሆንለታል።

Ver Capítulo Copiar




ማርቆስ 11:23
11 Referencias Cruzadas  

በጌታ ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።


ኢየሱስም ይህን በሰማ ጊዜ ብቻውን ገለል ወዳለ ቦታ በታንኳ ከዚያ ፈቀቅ አለ፤ ሕዝቡም ሰምተው ከየከተማው በእግር ተከተሉት።


እርሱም የእምነታችሁ ማነስ ነው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ተራራ “ከዚህ ወደዚያ ሂድ” ብትሉት ይሄዳል፤ የሚያቅታችሁ ምንም ነገርም የለም።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው “እውነት እላችኋለሁ፤ እምነት ካላችሁና ካልተጠራጠራችሁ፥ በበለሲቱ ዛፍ እንደተደረገው ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር’ ብትሉት ይሆናል፤


ጌታም አለ፦ “የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ፥ ይህን ሾላ ‘ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል፤’ ብትሉት፥ ይታዘዝላችሁ ነበር።


አብ በወልድ እንዲከብር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለሁ።


በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ፤ ይሆንላችሁማል።


ትንቢት የመናገር ስጦታ ቢኖረኝ፥ ምስጢርን ሁሉ ባውቅ፥ ዕውቀትን ሁሉ ብረዳ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos