Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማርቆስ 11:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ወደ ኢየሩሳሌም በደብረ ዘይት ተራራ አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረቡ ጊዜ፥ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ በማለት ላካቸው፦

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ወደ ኢየሩሳሌም በደብረ ዘይት ተራራ አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረቡ ጊዜ፣ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ በማለት ላካቸው፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሩሳሌም በቀረቡ ጊዜ በቤተ ፋጌና በቢታንያ አድርገው ወደ ደብረ ዘይት ደረሱ፤ ከዚያም ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ ሲል ላካቸው፦

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ወደ ኢየሩሳሌምም ከደብረ ዘይት አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረቡ ጊዜ፥ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ልኮ

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ወደ ኢየሩሳሌምም ከደብረ ዘይት አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረቡ ጊዜ፥ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ልኮ፦

Ver Capítulo Copiar




ማርቆስ 11:1
14 Referencias Cruzadas  

ኢየሱስ ግን ወደ ደብረዘይት ሄደ።


በዚያን ጊዜ ደብረዘይት ከሚባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ እርሱም ከኢየሩሳሌም የሰንበት መንገድ ያህል የራቀ ነው።


እርሱም ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን እንዲህ ሲል ላካቸው፤ “ወደ ከተማ ሂዱ፤ እንስራ ውሃ የተሸከመ ሰው ያገኛችኋል፤


ዐሥራ ሁለቱን ወደ እርሱ ጠርቶ፥ ሁለት ሁለቱን ላካቸው፤ በርኩሳን መናፍስትም ላይ ሥልጣን ሰጣቸው።


መዝሙር ከዘመሩ በኋላ ወደ ደብረዘይት ወጡ።


በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ፥ ደቀመዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው “እስቲ ንገረን፤ ይህ መቼ ይሆናል? የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድነው?” አሉት።


ትቶአቸውም ከከተማ ወጥቶ ወደ ቢታንያ ሄደ፤ በዚያም አደረ።


በዚያም ቀን የእግዚአብሔር እግሮች በኢየሩሳሌም ትይዩ በምሥራቅ በኩል ባለው በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ይቆማሉ፤ የደብረ ዘይት ተራራም በመካከሉ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ ይሰነጠቃል፥ እጅግም ጥልቅ ሸለቆ ይሆናል፤ የተራራውም እኩሌታ ወደ ሰሜን፥ እኩሌታውም ወደ ደቡብ ይሸሻል።


ኢየሱስ በቤተ መቅደሱ ትይዩ፥ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ጴጥሮስ፥ ያዕቆብ፥ ዮሐንስና እንድርያስ እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፤


ዳዊት ግን እያለቀሰ፥ ራሱን ተከናንቦ፥ ባዶ እግሩን የደብረ ዘይትን ተራራ ወጣ፤ አብሮት ያለውም ሕዝብ ሁሉ እንደዚሁ ራሱን ተከናንቦ እያለቀሰ ተራራውን ይወጣ ነበር።


በፊታችሁ ወዳለው መንደር ሂዱ፥ ሰው ተቀምጦበት የማያውቅ የአህያ ውርንጫ እዚያ ታስሮ ታገኛላችሁ፤ ፈታችሁ አምጡት፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios