Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 9:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስም የተደረገውን ነገር ሁሉ ሰማ፤ ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች፦ “ዮሐንስ ከሙታን ተነሣ፤”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስም፣ በዚህ ጊዜ የሆነውን ነገር ሁሉ ሰምቶ በሁኔታው ተደናገረ፤ ምክንያቱም አንዳንድ ሰዎች ዮሐንስ ከሙታን እንደ ተነሣ ያወሩ ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 አንዳንድ ሰዎች “መጥምቁ ዮሐንስ ከሞት ተነሥቶአል” እያሉ ያወሩ ስለ ነበረ የገሊላ አገረ ገዢ የነበረው ሄሮድስ ኢየሱስ ያደረገውን ሁሉ በመስማቱ ተደናገረ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የአ​ራ​ተ​ኛው ክፍል ገዥ ሄሮ​ድ​ስም የተ​ደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ሰምቶ የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ያጣ ነበር፤ መጥ​ምቁ ዮሐ​ንስ ከሙ​ታን ተለ​ይቶ ተነሣ የሚሉ ነበ​ሩና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የአራተኛው ክፍል ገዥ ሄሮድስም የተደረገውን ነገር ሁሉ ሰምቶ፥ አንዳንድ ሰዎች፦

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 9:7
13 Referencias Cruzadas  

እነርሱም መልሰው፦ “ ‘መጥምቁ ዮሐንስ፥’ ሌሎችም ‘ኤልያስ፥’ ሌሎችም ‘ከቀደሙት ነቢያት አንዱ ተነሥቶአል፤’ ይላሉ፤” አሉት።


ጢባርዮስ ቄሣር በነገሠ በዐሥራ አምስተኛው ዓመት፥ ጴንጤናዊው ጲላጦስም የይሁዳ ገዥ ነበር፥ ሄሮድስ የገሊላ አገረ ገዥ፥ ወንድሙ ፊልጶስ ደግሞ የኢጡርያስና የጥራኮኒዶስ አገረ ገዢ፥ ሊሳኒዮስም የአቢሊኒ አገረ ገዢ ሳሉ፥


ከእነርሱ የተሻለ የተባለው እንደ አሜከላ ነው፥ ቅን የተባለው እንደ ኩርንችት ነው፤ ጠባቂዎችህ የሚጐበኙበት ቀን መጥቷል፤ መሸበራቸውም አሁን ይሆናል።


ከሠራዊት ከጌታ በራእይ ሸለቆ ውስጥ የድንጋጤና የመረገጥ፥ ግራ የመጋባት፥ የቅጥር መፍረስና ወደ ተራራ ለእርዳታ የሚጮኽበት ቀን ሆኖአል።


እንዴት ለጥፋት ሆኑ! በድንገት አለቁ፥ በድንጋጤ ጠፉ።


“በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ላይ ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ በመረበሽ ይጨነቃሉ፤


ዮሐንስ በእስር ቤት ሳለ የክርስቶስን ሥራ ሰምቶ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለት ላከና


እነርሱም፥ “መጥምቁ ዮሐንስ የሚሉህ አሉ፤ ሌሎች ኤልያስ ነው ይሉሃል፤ ሌሎች ደግሞ ከነቢያት አንዱ ነው ይላሉ” ብለው ነገሩት።


በዚያን ሰዓት ከፈሪሳውያን አንዳንዶች ቀርበው “ሄሮድስ ሊገድልህ ይፈልጋልና ከዚህ ውጣና ሂድ፤” አሉት።


ከሄሮድስም ግዛት እንደመጣ ሲያውቅ፥ በዚያን ጊዜ በኢየሩሳሌም ተገኝቶ ወደነበረው ወደ ሄሮድስ ላከው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios