Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 4:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ለአርባ ቀን በዲያብሎስ ተፈተነ። በእነዚያም ቀኖች ምንም አልበላም፤ ቀኖቹም በተፈጸሙ ጊዜ ተራበ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በዚያም አርባ ቀን በዲያብሎስ ተፈተነ፤ በእነዚያም ቀናት ምንም ሳይበላ ከቈየ በኋላ በመጨረሻ ተራበ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እዚያም አርባ ቀን በዲያብሎስ ተፈተነ፤ በእነዚያም ቀኖች ምንም ስላልበላ በመጨረሻ ተራበ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 አርባ መዓ​ል​ትና አርባ ሌሊት ከዲ​ያ​ብ​ሎስ ተፈ​ተነ፥ በእ​ነ​ዚ​ያም ቀኖች ምንም አል​በ​ላም፤ እነ​ዚ​ያም ቀኖች ከተ​ፈ​ጸሙ በኋላ ተራበ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 አርባ ቀን ከዲያብሎስ ተፈተነ። በነዚያም ቀኖች ምንም አልበላም፥ ከተጨረሱም በኋላ ተራበ።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 4:2
16 Referencias Cruzadas  

ኤልያስም ተነሥቶ ምግቡን በላ፥ ውሃውንም ጠጣ፤ ከዚያም ምግብ ባገኘው ኃይል እስከ ተቀደሰው የሲና ተራራ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሙሉ ተጓዘ።


በዚያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከጌታ ጋር ነበረ፤ ምግብ አልበላም፥ ውኃም አልጠጣም። በጽላቶቹም ዓሥሩን የቃል ኪዳን ቃሎች ጻፈ።


እኛ ያለን ሊቀ ካህናት በድካማችን ሊራራልን የሚችል ነው፤ እርሱ በሁሉ ነገር እንደ እኛ ተፈተነ፤ ሆኖም ምንም ኃጢአት አልሠራም።


ምክንያቱም እርሱ ራሱ ተፈትኖ መከራን ስለ ተቀበለ የሚፈተኑትን ሊረዳቸው ይችላል።


የድንጋዩን ጽላቶች፥ ጌታ ከእናንተ ጋር ቃል ኪዳን የፈጸመባቸውን ጽላቶች፥ ለመቀበል ወደ ተራራ በወጣሁ ጊዜ፥ በተራራው አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ተቀምጬ ነበር፤ እህል አልቀመስኩም፥ ውኃም አልጠጣሁም።


በዚያም የያዕቆብ ጉድጓድ ነበረ። ኢየሱስም መንገድ ከመሄድ ደክሞ በጉድጓድ አጠገብ ተቀመጠ፤ ጊዜውም ስድስት ሰዓት ያህል ነበረ።


ከዚህም በኋላ እንደገና አርባ ቀንና አርባ ሌሊት እህል ሳልቀምስና ውኃ ሳልጠጣ በጌታ ፊት በግንባሬ ተደፍቼ ቆየሁ። ይህንንም ያደረግኹት ስለ ሠራችሁት ኃጢአት ሁሉ፥ እርሱንም ለማስቆጣት በጌታ ፊት ክፉ የሆነውን ነገር ስላደረጋችሁ ነበር።


በማለዳም ወደ ከተማ ሲመለስ ራበው።


አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ።


በነነዌ ሁሉ ይህንን አዋጅ አስነገረ፦ በንጉሡና በመኳንንቱ ትእዛዝ መሠረት፥ ሰውም ሆነ እንስሳ፥ ከብትም ሆነ በግ አንዳች አይቅመሱ፤ አይሰማሩ፥ ውኃም አይጠጡ፥


ፍልስጥኤማዊውም አርባ ቀን ሙሉ ጠዋትና ማታ እየመጣ በመቆም ይታያቸው ነበር።


“አጠፋችኋለሁ፥ ብሎ ጌታም ስለ ተናገረ፥ በግንባሬ ተደፍቼ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በጌታ ፊት ወደቅሁ።


ሙሴም ወደ ደመናው ውስጥ ገባ ወደ ተራራውም ወጣ፤ ሙሴም በተራራው ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቆየ።


“በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ “በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፥ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትነድፋለህ።”


ዲያብሎስም፦ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ ይህን ድንጋይ እንጀራ እንዲሆን እዘዝ፤” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios