ሉቃስ 14:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 አገልጋዩም መልሶ ይህንን ለጌታው ነገረው። በዚያን ጊዜ ባለቤቱ ተቆጥቶ አገልጋዩን ‘ወደ ከተማ ጎዳናና ወደ ስላች መንገዶች ውጣ፤ ድሆችንና ጉንድሾችን ና ዐይነ ስውሮችንና አንካሶችንም ወደዚህ አስገባ፤’ አለው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 “ባሪያውም ተመልሶ መጥቶ ይህንኑ ለጌታው ነገረው። በዚህ ጊዜ የቤቱ ጌታ ተቈጥቶ አገልጋዩን፣ ‘ቶሎ ብለህ ወደ ከተማው አውራ ጐዳናዎችና መተላለፊያ መንገዶች ውጣ፤ ድኾችንና አካለ ስንኩሎችን፣ ዐይነ ስውሮችንና ዐንካሶችን ወደዚህ አስገባቸው’ አለው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 “አገልጋዩም ወደ ቤት ተመልሶ ይህን ሁሉ ለጌታው ነገረው፤ የቤቱም ጌታ ተቈጥቶ አገልጋዩን ‘ቶሎ ብለህ ወደ ከተማው ጐዳናዎችና ስላች መንገዶች ሂድ፤ ድኾችን፥ አካለ ስንኩሎችን፥ ዕውሮችን፥ አንካሶችንም ጠርተህ አምጣልኝ’ አለው። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 አገልጋዩም ተመልሶ ለጌታው ይህንኑ ነገረው፤ ያንጊዜም ባለቤቱ ተቈጣ፤ አገልጋዩንም፦ ፈጥነህ ወደ አደባባይና ወደ ከተማው ጐዳና ሂድ፤ ድሆችንና ጦም አዳሪዎችን፥ ዕውሮችንና አንካሶችን ወደዚህ አምጣልኝ አለው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 ባሪያውም ደርሶ ይህን ለጌታው ነገረው። በዚያን ጊዜ ባለቤቱ ተቆጥቶ ባሪያውን፦ ወደ ከተማ ጎዳናና ወደ ስላች ፈጥነህ ውጣ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንና ዕውሮችንም ወደዚህ አግባ አለው። Ver Capítulo |