Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 13:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እነሆም፥ ከዐሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ርኩስ መንፈስ በሽተኛ ያደረጋት አንዲት ሴት ነበረች፤ እርሷም ጎባጣ ነበረች፤ ቀጥ ብላ መቆምም በፍጹም አልተቻላትም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በዚያም የድካም መንፈስ ዐሥራ ስምንት ዓመት ሙሉ አካለ ስንኩል ያደረጋት አንዲት ሴት ነበረች፤ እርሷም ከመጕበጧ የተነሣ ፈጽሞ ቀና ማለት አትችልም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከዚያም ከዐሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ ርኩስ መንፈስ ጀርባዋን ያጐበጣት አንዲት ሴት ነበረች፤ እርስዋ ወገብዋ በመጒበጡ ቀና ለማለት በፍጹም አትችልም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ዐሥራ ስም​ንት ዓመት ሙሉ ጋኔን ያጐ​በ​ጣት አን​ዲት ሴት ነበ​ረች፤ ጐባ​ጣም ነበ​ረች፤ ከቶ ቀጥ ብላ መቆም አት​ች​ልም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እነሆም፥ ከአሥራ ስምንት ዓመት ጀምሮ የድካም መንፈስ ያደረባት ሴት ነበረች፥ እርስዋም ጐባጣ ነበረች ቀንታም ልትቆም ከቶ አልተቻላትም።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 13:11
20 Referencias Cruzadas  

ከክፉዎች መናፍስትና ከደዌም ተፈውሰው የነበሩ አንዳንድ ሴቶች፤ ከእነርሱም፦ ሰባት አጋንንት የወጡላት መግደላዊት የምትባል ማርያም፥


ይህች ለዐሥራ ስምንት ዓመት ሰይጣን ያሠራት የአብርሃም ልጅ በሰንበት ቀን ከዚህ እስራት ልትፈታ አይገባምን? አለው።


እርሱም ወደ ምድር እንደ ወረደ አጋንንት ያደሩበት አንድ ሰው ከከተማ ወጥቶ ተገናኘው፤ ለረጅም ጊዜ ልብስ አይለብስም ነበር፥ በመቃብሮች እንጂ በቤት ውስጥም አይኖርም ነበር።


አቤቱ፥ በቁጣህ አትቅሠፈኝ፥ በመዓትህም አትገሥጸኝ።


ይህ የመፈወስ ምልክት የተደረገለት ሰው ከአርባ ዓመት ይበልጠው ነበርና።


ከዐሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፤ ያላትንም ንብረት ሁሉ ተጠቅማ ለባለመድኃኒቶች ብታውልም ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም።


ኢየሱስም የልጁን አባት፥ “ከያዘው ስንት ጊዜው ነው?” ብሎ ጠየቀው። እርሱም እንዲህ አለው፤ “ከሕፃንነቱ ጀምሮ ነው፤


ጌታ የዕውሮችን ዐይን ያበራል፥ ጌታ የወደቁትን ያነሣል፥ ጌታ ጻድቃንን ይወድዳል፥


ወደ መቅደስም ከሚገቡት ምጽዋት ይለምን ዘንድ፥ ሰዎች ተሸክመው መልካም በሚሉአት በመቅደስ ደጅ በየቀኑ ያስቀምጡት የነበሩ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ አንካሳ የሆነ አንድ ሰው ነበረ።


ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰሰች፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና፥ በዓል የሚያከብሩ ሰዎች የደስታና ምስጋና ቃል አሰሙ።


ከአላዋቂነቴ የተነሣ ቁስሌ ሸተተ በሰበሰም፥


ሰይጣንም ከጌታ ፊት ወጣ፥ ኢዮብንም ከእግሩ መርገጫ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ በክፉ ቁስል መታው።


ጌታ በቃሎቹ የታመነ ነው፥ በሥራውም ሁሉ ጻድቅ ነው፥ ጌታ የሚወድቁትን ሁሉ ይደግፋቸዋል፥ ያጎነበሱትንም ያነሣቸዋል።


ኢየሱስም በምኵራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትን ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝቡ መካከል ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዘዋወር ነበር።


ኢየሱስም ባያት ጊዜ ጠራትና “አንቺ ሴት! ከበሽታሽ ተፈውሰሻል፤” አላት፤


ይህም መሆን ሲጀምር መዳናችሁ ቀርቦአልና ቁሙ፤ ቀናም በሉ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios