ዘሌዋውያን 27:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 “ሰውም ከርስቱ እርሻ ለጌታ ቢቀድስ፥ ግምትህ ለእርሻው እንደሚያስፈልገው የዘር መጠን ይሁን፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ገብስ የሚዘራበት እርሻ ኀምሳ የብር ሰቅል ይገመታል። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 “ ‘አንድ ሰው ከወረሰው ርስት ላይ ለእግዚአብሔር የዕርሻ መሬት ቢቀድስ፣ ዋጋው የሚተመነው ለመሬቱ በሚያስፈልገው ዘር መጠን ይሆናል፤ ይኸውም ለአንድ ሆሜር መስፈሪያ የገብስ ዘር ዐምሳ ሰቅል ጥሬ ብር ነው። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 “አንድ ሰው ከመሬቱ ከፍሎ ለእግዚአብሔር የተለየ ስጦታ አድርጎ ቢያቀርብ፥ ዋጋው መሬቱ በሚቀበለው ዘር መጠን ይወሰን፤ ይኸውም ለእያንዳንዱ ኪሎ ግራም ገብስ ተቀባይ መሬት ኀምሳ ጥሬ ብር ይክፈል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 “ሰውም ከርስቱ እርሻ ለእግዚአብሔር ቢሳል፥ እንደ መዘራቱ መጠን ይገመት፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ገብስ የሚዘራበት እርሻ አምሳ ወቄት ብር ይገመታል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ሰውም ከርስቱ እርሻ ለእግዚአብሔር ቢቀድስ፥ እንደ መዘራቱ መጠን ይገመት፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ገብስ የሚዘራበት እርሻ አምሳ የብር ሰቅል ይገመታል። Ver Capítulo |