መሳፍንት 9:49 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)49 ሰዎቹም ሁሉ ቅርንጫፎች ቈርጠው አቤሜሌክን ተከተሉት፤ ቅርንጫፎቹንም ምሽጉ ላይ አስደግፈው በመከመር ሰዎቹ በውስጡ እንዳሉ በእሳት አቃጠሏቸው። ስለዚህ በሴኬም ምሽግ ውስጥ የነበሩት አንድ ሺህ ያህል ወንዶችና ሴቶች ሞቱ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም49 ሰዎቹም ሁሉ ቅርንጫፎች ቈርጠው አቢሜሌክን ተከተሉት፤ ቅርንጫፎቹንም ምሽጉ ላይ አስደግፈው በመከመር ሰዎቹ በውስጡ እንዳሉ በእሳት አቃጠሏቸው። ስለዚህ በሴኬም ግንብ ውስጥ የነበሩት አንድ ሺሕ ያህል ወንዶችና ሴቶች ሞቱ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም49 እያንዳንዱም ሰው ከዛፍ እንጨት ቈረጠ፤ አቤሜሌክንም ተከትለው ያን እንጨት ምሽጉን በማስደገፍ ከመሩት፤ ሰዎቹ በውስጡ እንዳሉም በእሳት አቃጠሉት፤ ስለዚህም በምሽጉ ውስጥ የነበሩት ሰዎች ሁሉ ሞቱ፤ የወንዶቹና የሴቶቹ ቊጥር አንድ ሺህ ያኽል ነበር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)49 ሕዝቡም ሁሉ እንዲሁ እያንዳንዳቸው የዛፉን ቅርንጫፎች ቈረጡ፤ አቤሜሌክንም ተከትለው በምሽጉ ዙሪያ አኖሩአቸው፤ ምሽጉንም በላያቸው በእሳት አቃጠሉት፤ የሰቂማም ግንብ ሰዎች ሁሉ ደግሞ አንድ ሺህ የሚያህሉ ወንድና ሴት ሞቱ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)49 ሕዝቡም ሁሉ እንዲሁ እያንዳንዳቸው የዛፉን ቅርንጫፎች ቈረጡ፥ አቤሜሌክንም ተከትለው በምሽጉ ዙሪያ አኖሩአቸው፥ ምሽጉንም በላያቸው አቃጠሉት፥ የሴኬምም ግንብ ሰዎች ሁሉ ደግሞ አንድ ሺህ የሚያህሉ ወንድና ሴት ሞቱ። Ver Capítulo |