መሳፍንት 7:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 የሦስት መቶው ቀንደ መለከት ድምፅ እንደተሰማም ጌታ በሰፈሩ ውስጥ ያለው ሰው አንዱ በሌላው ላይ ሰይፉን እንዲመዝበት አደረገ፤ ሠራዊቱ በጽሬራ አቅጣጫ እስከ ቤትሺጣ፥ ከዚያም አልፈው በጠባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልመሖላ ድንበር ድረስ ሸሽተው ሄዱ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 የሦስት መቶው ቀንደ መለከት ድምፅ እንደ ተሰማም እግዚአብሔር በሰፈሩ ውስጥ ያለው ሰው አንዱ በሌላው ላይ ሰይፉን እንዲመዝበት አደረገ፤ ሰራዊቱ በጽሬራ አቅጣጫ ወደ ቤትሺጣ፣ ከዚያም ዐልፈው በጠባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልምሖላ ድንበር ድረስ ሸሽተው ሄዱ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ሦስት መቶው የጌዴዎን ሰዎች እምቢልታቸውን በሚነፉበት ጊዜ እግዚአብሔር እያንዳንዱን የጠላት ወታደር በጓደኛው ላይና በሠራዊቱ ላይ ሰይፉን እንዲያነሣ አደረገ፤ ሠራዊቱም ፊታቸውን ወደ ጽሬራ በመመለስ እስከ ቤትሺጣ፥ ከዚያም አልፎ በጣባት አጠገብ እስካለው አቤልመሖላ ድረስ ሸሽተው ሄዱ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ሦስቱንም መቶ ቀንደ መለከቶችን ነፉ፤ እግዚአብሔርም የሰውን ሁሉ ሰይፍ በባልንጀራዉና በሠራዊቱ ሁሉ ላይ አደረገ፤ ሠራዊቱም በጽሬራ በኩል እስከ ቤትሲጣ ጋራጋታ ድረስ በጣባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልሜሁላ ዳርቻ ድረስ ሸሸ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ሦስቱንም መቶ ቀንደ መለከቶች ነፉ፥ እግዚአብሔርም የሰውን ሁሉ ሰይፍ በባልንጀራውና በሠራዊቱ ሁሉ ላይ አደረገ፥ ሠራዊቱም በጽሬራ በኩል እስከ ቤትሺጣ ድረስ በጠባት አጠገብ እስካለው እስከ አቤልምሖላ ዳርቻ ድረስ ሸሸ። Ver Capítulo |