Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 6:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እስራኤላውያን ዘር በሚዘሩበት ጊዜ ሁሉ ምድያማውያን፥ አማሌቃውያንና ሌሎች የምሥራቅ ሕዝቦች መጥተው አገሩን ይወሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እስራኤላውያን ዘር በሚዘሩበት ጊዜ ሁሉ ምድያማውያን፣ አማሌቃውያንና ሌሎች የምሥራቅ ሕዝቦች መጥተው አገሩን ይወሩ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እስራኤላውያን ዘር በሚዘሩበት ጊዜ ምድያማውያን፥ ከዐማሌቃውያንና የምሥራቅ ሰዎች እየመጡ አደጋ ይጥሉባቸው ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዘር በዘሩ ጊዜ ምድ​ያ​ማ​ው​ያ​ንና አማ​ሌ​ቃ​ው​ያን ይዘ​ም​ቱ​ባ​ቸው ነበር፥ በም​ሥ​ራ​ቅም የሚ​ኖሩ ልጆች አብ​ረው ይዘ​ም​ቱ​ባ​ቸው ነበር፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እስራኤልም ዘር በዘሩ ጊዜ ምድያማውያን አማሌቃውያንም በምሥራቅም የሚኖሩ ሰዎች ይመጡባቸው ነበር፥

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 6:3
25 Referencias Cruzadas  

ብዛታቸው እንደ አንበጣ መንጋ የሆነ ምድያማውያን፥ አማሌቃውያንና ሌሎችም የምሥራቅ ሕዝቦች በሸለቆው ውስጥ ሰፍረው ነበር፤ የግመሎቻቸውም ብዛት በባሕር ዳርቻ እንዳለ አሸዋ ስፍር ቍጥር አልነበረውም።


በዚህ ጊዜ ምድያማውያን ሁሉ፥ አማሌቃውያንና ሌሎች የምሥራቅ ሕዝቦች ያላቸውን አስተባብረው የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር በኢይዝራኤል ሸለቆ ሰፈሩ።


እርሱም አሞናውያንንና አማሌቃውያንን ካስተባበረ በኋላ እስራኤልን ወግቶ የዘንባባ ዛፎችበ ከተማ የሆነችውን ኢያሪኮን ያዙ።


ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎች፥ አምስት መቶ እንስት አህዮችና እጅግ ብዙም አገልጋዮች ነበሩት። ያም ሰው በምሥራቅ ካሉ ሰዎች ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነበረ።


ሰሎሞን ከምሥራቅ አገርና ከግብጽም ጥበበኞች እጅግ የላቀ ጥበብ ነበረው።


በዚህ ጊዜ ዜባሕና ጻልሙና ዐሥራ አምስት ሺህ ከሆነ ሠራዊታቸው ጋር ቀርቀር በተባለ ስፍራ ነበሩ፤ ይህም ከምሥራቅ ሕዝቦች ከተውጣጣውና በጦር ሜዳ ከወደቀው መቶ ሃያ ሺህ ሰይፍ ታጣቂ ሠራዊት የተረፈው ነበር።


ያዕቆብም ተነሥቶ ወደ ምሥራቅ ሰዎች አገር ሄደ።


ትዘራለህ፥ ነገር ግን አታጭድም፤ ወይራ ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን ዘይቱን አትቀባም፤ ወይን ትጨምቃለህ፥ ነገር ግን የወይን ጠጁን አትጠጣም።


እኔ ልዝራ፥ ሌላ ሰውም ይብላው፥ የሚበቅለውም ሁሉ ይነቀል።”


እስክትጠፋም ድረስ የከብትህን ፍሬና የምድርህን ፍሬ ይበላል፤ እስኪያጠፋህም ድረስ የእህል፥ የወይን ወይም የዘይት፥ የከብትህን ጥጃ ወይም የበግና ፍየል መንጋህን አይተውልህም።


እኔ ደግሞ እንዲህ አደርግባችኋለሁ፤ ፍርሃትን፥ ነፍስን የሚያኮስስና ዓይንን የሚያፈዝዝ ክሳትና ትኩሳት አመጣባችኋለሁ፤ ጠላቶቻችሁም ይበሉታልና ዘራችሁን በከንቱ ትዘራላችሁ።


እስራኤላውያን የምድያማውያን ኃይል ስለበረታባቸው በየዋሻውና በየምሽጉ፥ በየተራራው ጥግ መሸሸጊያ ስፍራ አበጁ።


እነርሱም በምድሪቱ ላይ ሰፍረው እስከ ጋዛ ያለውን ሰብል በማጥፋት አንዳችም የእህልዘር አያስተርፉም፥ የበግም ሆነ የከብት ወይም የአህያ መንጋ አይተዉም ነበር።


እስራኤላውያንም ተጠርተው ከሚያስፈልጋቸው ስንቅና ትጥቅ ጋር ለጦርነት ተዘጋጁ፤ እነርሱም ወደ ጦርነቱ በመዝመት በሁለት ቡድን ተከፍለው ከሶርያውያን ፊት ለፊት ባለው ቦታ ሰፈሩ፤ የእስራኤል ወታደሮች ቍጥር አገሩን ካጥለቀለቀው ከሶርያውያን ሠራዊት ብዛት ጋር ሲነጻጸር ከሁለት የተከፈሉ የጥቂት ፍየሎች መንጋዎች ይመስሉ ነበር።


ጌታ፦ ከእንግዲህ ወዲህ በእርግጥ ለጠላቶችሽ መብል ይሆን ዘንድ እህልሽን አልሰጥም፥ መጻተኞችም የደከምሽበትን ወይንሽን አይጠጡም፤


ስለዚህ እነሆ ርስት አድርጌ ለምሥራቅ ልጆች አሳልፌ እሰጥሻለሁ፥ እነርሱም በአንቺ ውስጥ ይሰፍራሉ፥ ማደሪያዎቻቸውንም በአንቺ ውስጥ ይሠራሉ፤ ፍሬሽን ይበላሉ ወተትሽንም ይጠጣሉ።


ነገር ግን የአብርሃም ለነበሩትም ለቁባቶቹ ልጆች አብርሃም ስጦታ ሰጣቸው፥ እርሱም ገና በሕይወቱ ሳለ ከልጁ ከይስሐቅ ለይቶ ወደ ፀሐይ መውጫ ወደ ምሥራቅ አገር ሰደዳቸው።


አማሌቅም መጥቶ በረፊድም ከእስራኤል ጋር ተዋጋ።


ሲዶናውያን፥ አማሌቃውያንና ማዖናውያን አሠቃዩአችሁ፤ እናንተም እንድረዳችሁ ወደ እኔ ጮኻችሁ፤ ታዲያ እኔ ከእጃቸው አላዳንኋችሁምን?


በዚህ ዓይነት ኪራም ለሰሎሞን የሚያስፈልገውን የሊባኖስን ዛፍና የዝግባ ግንድ ሁሉ አቀረበለት።


በምዕራብ በኩል በፍልስጥኤም ተረተር ላይ ይወርዳሉ፤ ሁለቱም ተባብረው በምሥራቅ ያለውን ሕዝብ ይዘርፋሉ፤ በኤዶምና በሞዓብ ላይ እጃቸውን ያነሣሉ፤ አሞናውያንም ይገዙላቸዋል።


የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ድል ስላደረጋቸው ስለ ቄዳርና ስለ አሦር መንግሥታት፤ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ተነሡ ወደ ቄዳርም ውጡ፥ የምሥራቅንም ልጆች አጥፉ።


ለአሞንም ልጆች እንዲህ በላቸው፦ የጌታ እግዚአብሔርን ቃል ስሙ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መቅደሴ በረከሰ ጊዜ፥ የእስራኤልም ምድር ባድማ በሆነች ጊዜ፥ የይሁዳም ቤት ተማርከው በተወሰዱ ጊዜ እሰይ ብለሻልና፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios