Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 5:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የይሳኮርም አለቆች ከዲቦራ ጋር ነበሩ፥ ይሳኮርም እንደ ባራቅ ነበረ፥ ከእግሩ በኋላ ወደ ሸለቆው ቸኰሉ፥ በሮቤል ፈሳሾች አጠገብ ብዙ የልብ ማመንታት ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የይሳኮር መሳፍንት ከዲቦራ ጋራ ነበሩ፤ ይሳኮርም ራሱ ወደ ሸለቆው ከኋላው በመከተል፣ ከባርቅ ጋራ ነበረ። በሮቤል አውራጃዎች፣ ብዙ የልብ ምርምር ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 የይሳኮር መሪዎች ከዲቦራ ጋር መጡ፤ አዎ፥ ይሳኮርም ባራቅም መጡ፤ ወደ ሸለቆው ተከተሉት፤ ነገር ግን የሮቤል ነገድ ለሁለት ተከፈለ፤ ለመምጣት ወይም ላለመምጣት አመነታ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የይ​ሳ​ኮ​ርም አለ​ቆች ከዲ​ቦራ ጋር ነበሩ፤ ይሳ​ኮ​ርም እንደ ባርቅ ነበረ፤ ከእ​ግሩ በኋላ ወደ ሸለ​ቆው ቸኮሉ፤ በሮ​ቤል ፈሳ​ሾች አጠ​ገብ ብዙ የልብ ማመ​ን​ታት ነበረ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 የይሳኮርም አለቆች ከዲቦራ ጋር ነበሩ፥ ይሳኮርም እንደ ባርቅ ነበረ፥ ከእግሩ በኋላ ወደ ሸለቆው ቸኰሉ፥ በሮቤል ፈሳሾች አጠገብ ብዙ የልብ ማመንታት ነበረ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 5:15
10 Referencias Cruzadas  

በዚህ ጊዜ ዲቦራ ባራቅን፥ “ተነሣ! ጌታ ሲሣራን በእጅህ አሳልፎ የሰጠባት ቀን ይህች ናት፤ እነሆ ጌታ በፊትህ ቀድሞ ወጥቶአል” አለችው። ስለዚህ ባራቅ ዐሥር ሺህ ሰዎችን አስከትሎ ከታቦር ተራራ ወረደ።


እንደ አንዲት ንጽሕት ድንግል እናንተን ለክርስቶስ ለማቅረብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለሁና፥ በእግዚአብሔር ቅንዐት እቀናላችኋለሁና።


እኛ ግን ጳውሎስን ከዚያ እንቀበለው ዘንድ ስላለን ወደ መርከብ ቀድመን ሄድንና ወደ አሶን ተነሣን፤ እርሱ በመሬት ይሄድ ዘንድ ስላሰበ እንደዚህ አዞ ነበርና።


ስለዚህም እርስ በርሳቸው እስኪለያዩ ድረስ መከፋፋት ሆነ፥ በርናባስም ማርቆስን ይዞ በመርከብ ወደ ቆጵሮስ ሄደ።


ሰነፍ ሰው፦ “ውጪ አንበሳ አለ፤ ብወጣ፥ በመንገዱ ላይ እሞታለሁ” ይላል።


እስራኤልም የሚገባውን እንዲፈጽም የዘመኑን ሁኔታ የሚያውቁ ጥበበኞች ሰዎች የይሳኮር ልጆች አለቆች ሁለት መቶ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ሁሉ ይታዘዙአቸው ነበር።


ባራቅ ለዛብሎንና ለንፍታሌም ሰዎች ጥሪ አስተላለፈ፤ ዐሥር ሺህ ሰዎች ተከተሉት፤ ዲቦራም አብራው ሄደች።


ዲቦራ በንፍታሌም ውስጥ ቃዴስ በተባለች ከተማ ይኖር የነበረውን የአቢኒኤምን ልጅ ባራቅን አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ሲል ያዝሃል፤ ‘ተነሣ፤ ከንፍታሌምና ከዛብሎን ዐሥር ሺህ ሰዎች ይዘህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤


መንጎች ሲያፍዋጩ ለመስማት በበጎች ጉረኖ መካከል ለምን ተቀመጥህ? በሮቤል ፈሳሾች አጠገብ ታላቅ የልብ ምርምር ነበረ።


የልያ ልጆች፥ የያዕቆብ በኩር ልጅ ሮቤል፥ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዛብሎን፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios