Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 2:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ያንን ስፍራ ቦኪምሠ ብለው ጠሩት፤ በዚያም ለጌታ መሥዋዕት አቀረቡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ያን ስፍራ ቦኪም ብለው ጠሩት፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ያ ስፍራ “ቦኪም” ተብሎ የተጠራውም በዚህ ምክንያት ነው፤ በዚያም ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረቡ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የዚ​ያም ስፍራ ስም “መካነ ብካይ” ተብሎ ተጠራ፤ በዚ​ያም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠዉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የዚያንም ስፍራ ስም ቦኪም ብለው ጠሩት፥ በዚያም ለእግዚአብሔር ሠዉ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 2:5
8 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ሳሙኤል አንድ የሚጠባ የበግ ግልገል ወስዶ ሙሉ ለሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ ለጌታ አቀረበው፤ ስለ እስራኤልም ወደ ጌታ ጸለየ፤ ጌታም መለሰለት።


ማኑሄም የፍየሉን ጠቦት ከእህል ቁርባኑ ጋር ወስዶ በዐለት ላይ ለጌታ ሠዋው። ማኑሄና ሚስቱ እያዩ ጌታ አስደናቂ ነገር አደረገ፤


ጌዴዎንም በዚያ ለጌታ መሠዊያ ሠራ፤ ስሙንም “ጌታ ሰላም ነው” ብሎ ጠራው፤ ይህ መሠዊያ የአቢዔዝራውያን ይዞታ በሆነው በዖፍራ ዛሬም ቆሞ ይታያል።


በእርሱም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ ያለ ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩ፤ ጌታም ከጽኑ ቁጣው ተመለሰ። ስለዚህም የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ የአኮር ሸለቆ ተብሎ ተጠራ።


የርብቃ ሞግዚት ዲቦራም ሞተች፥ በቤቴልም ከባሉጥ ዛፍ በታች ተቀበረች፥ ስሙም “አሎንባኩት” ተብሎ ተጠራ።


የጌታ መልአክ ከጌልገላ ወደ ቦኪም ወጥቶ እንዲህ አለ፤ “ከግብጽ ምድር አወጣኋችሁ፤ ለቀደሙትም አባቶቻችሁ ልሰጣቸው ወደ ማልሁላቸው ምድር አመጣኋችሁ፤ እንዲህም አልሁ፤ ከእናንተ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን አላፈርስም፤


የጌታም መልአክ ይህን ቃል ለእስራኤል ልጆች ሁሉ በተናገረ ጊዜ ሕዝቡ ድምፃቸውን አንሥተው አለቀሱ።


ኢያሱ ሕዝቡን ካሰናበተ በኋላ እያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ ምድሪቱን ለመውረስ ወደ የርስቱ ሄደ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios