መሳፍንት 19:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 ሆኖም ሰዎቹ ሊሰሙት አልፈለጉም፤ ስለዚህ ሌዋዊው ቁባቱን ወደ ውጭ አወጣላቸው፤ ሰዎቹም አመነዘሩባት፤ ሌሊቱን ሙሉ ሲፈራረቁባት አድረው ጐሕ ሲቀድ ለቀቋት። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም25 ሆኖም ሰዎቹ ሊሰሙት አልፈለጉም፤ ስለዚህ ሌዋዊው ቁባቱን ወደ ውጭ አወጣላቸው፤ ሰዎቹም አመነዘሩባት፤ ሌሊቱን ሙሉ ሲፈራረቁባት ዐድረው ጎሕ ሲቀድ ለቀቋት። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 ሰዎቹ ግን አልሰሙትም፤ ስለዚህ ሰውዬው ቊባቱን ወደ ውጪ አውጥቶ ሰጣቸው፤ ሌሊቱንም ሙሉ በእርስዋ ላይ ተራ በተራ በማመንዘር መጫወቻ አድርገዋት ዐደሩ፤ ሲነጋጋ ግን እንድትሄድ ለቀቁአት። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 ሰዎቹ ግን ሊሰሙት አልፈቀዱም፤ ሰውየውም ዕቅብቱን ይዞ ወደ እነርሱ አወጣላቸው፤ አዋረድዋትም፤ ሌሊቱንም ሁሉ እስኪነጋ ድረስ አመነዘሩባት፤ ጎህም በቀደደ ጊዜ ለቀቁአት። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 ሰዎቹ ግን ነገሩን አልሰሙም፥ ሰውዮውም ቁባቱን ይዞ አወጣላቸው፥ ደረሱባትም፥ ሌሊቱንም ሁሉ እስኪነጋ ድረስ አመነዘሩባት፥ ጎህ በቀደደም ጊዜ ለቀቁአት። Ver Capítulo |