Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 19:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ወደ የቡስ እንደ ቀረቡም ጊዜው እየመሸ ስለ ነበር አገልጋዩ ጌታውን፥ “እንግዲህ ወደዚህች ወደ የቡሳውያን ከተማ ጐራ ብለን እንደር” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ወደ ኢያቡስ እንደ ቀረቡም ጊዜው እየመሸ ስለ ነበር አገልጋዩ ጌታውን፣ “እንግዲህ ወደዚህች ወደ ኢያቡሳውያን ከተማ ጐራ ብለን እንደር” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ወደ ኢያቡስ በደረሱ ጊዜ መሸባቸው፤ አሽከሩም ጌታውን “ና እባክህ ወደ እዚህ ወደ ኢያቡሳውያን ከተማ እንመለስና እዚያ እንደር” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በኢ​ያ​ቡ​ስም አን​ጻር ገና ሳሉ ፀሐ​ይዋ ተቈ​ለ​ቈ​ለች፤ ብላ​ቴ​ና​ውም ጌታ​ውን፥ “ና፤ ወደ​ዚ​ህች ወደ ኢያ​ቡ​ሳ​ው​ያን ከተማ፥ እባ​ክህ እና​ቅና፤ በእ​ር​ስ​ዋም እን​ደር” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ወደ ኢያቡስም በደረሱ ጊዜ መሸባቸው፥ አሽከሩም ጌታውን፦ ና፥ ወደዚህ ወደ ኢያቡሳውያን ከተማ፥ እባክህ፥ እናቅና፥ በእርስዋም እንደር አለው።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 19:11
8 Referencias Cruzadas  

ሌሎቹም የከነዓን ዘሮች ኢያቡሳውያን፥ አሞራውያን፥ ጌርጌሳውያን፥


ንጉሡና ሰዎቹ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን ለመውጋት ወደዚያ ዘመቱ። እነርሱም፥ “ዳዊት እዚህ ሊገባ አይችልም” ብለው ስላሰቡ ዳዊትን፥ “ዕውሮችና አንካሶች እንኳ ስለሚከላከሉህ ወደዚህች አትገባም” አሉት።


ኢያቡሳዊውን፥ አሞራዊውን፥ ጌርጌሳዊውን፥


በኢየሩሳሌም የተቀመጡትን ኢያቡሳውያንን ግን የይሁዳ ልጆች ሊያሳድዱአቸው አልቻሉም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ በይሁዳ ልጆች መካከል በኢየሩሳሌም ውስጥ ተቀምጠዋል።


ነገር ግን የብንያም ሰዎች በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን ከዚያ አላስወጧቸውም፤ ስለዚህ ኢያቡሳውያን እስከ ዛሬ ድረስ ከብንያማውያን ጋር በዚያ አብረው ይኖራሉ።


ሌዋዊው ግን በዚያች ሌሊት በዚያ ለማደር ስላልፈለገ ተነሥቶ የተጫኑትን ሁለቱን አህዮቹንና ቁባቱን ይዞ ኢየሩሳሌም ወደተባለችው ወደ የቡስ ሄደ።


ጌታውም፥ “አይሆንም፤ ሕዝቧ እስራኤላዊ ወዳልሆነ ወደ ባዕድ ከተማ አንገባም፤ ወደ ጊብዓ አልፈን እንሂድ” አለው።


ለአህዮቻችን ገለባና ገፈራ አለን፤ እኛ ባሮችህ ለእኔም ሆነ ለገረድህ፥ አብሮን ላለውም ወጣት እንጀራና የወይን ጠጅ ይዘናል፤ ሌላ ምንም ነገር አያስፈልገንም።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos