Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መሳፍንት 17:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ሚካም፥ “እንግዲያውስ አብረኸኝ ተቀመጥ፤ አባትም ካህንም ሁነኝ፤ እኔም በዓመት ዐሥር ሰቅል ብር እንዲሁም ልብስና ምግብ እሰጥሃለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ሚካም፣ “እንግዲያውስ ዐብረኸኝ ተቀመጥ፤ አባትም ካህንም ሁነኝ፤ እኔም በዓመት ዐሥር ሰቅል ብር እንዲሁም ልብስና ምግብ እሰጥሃለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሚካም “እንግዲያውስ ከእኔ ጋር ኑር፤ የእኔ አማካሪና ካህን ሁንልኝ፤ በዓመት ዐሥር ብር እንዲሁም ልብስና ምግብ እሰጥሃለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሚካም፥ “በእኔ ዘንድ ተቀ​መጥ፤ አባ​ትና ካህ​ንም ሁነኝ፤ እኔም ልብ​ሶ​ች​ንና ምግ​ብ​ህን፥ በየ​ዓ​መ​ቱም ዐሥር ብር እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ሚካም፦ ከእኔ ዘንድ ተቀመጥ፥ አባትና ካህንም ሁነኝ፥ እኔም ልብሶችንና ምግብህን፥ በየዓመቱም አሥር ብር እሰጥሃለሁ አለው። ሌዋዊውም ገባ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 17:10
17 Referencias Cruzadas  

አሁንም እናንተ ወደዚህ የላካችሁኝ አይደላችሁም፥ እግዚአብሔር ላከኝ እንጂ፥ ለፈርዖንም እንደ አባት አደረገኝ፥ በቤቱምም ሁሉ ላይ ጌታ፥ በግብጽ ምድርም ሁሉ ላይ አለቃ አደረገኝ።


ነቢዩ ኤልሳዕ በብርቱ ደዌ ታሞ ነበር፤ ተኝቶም ሊሞት በሚያጣጥርበት ጊዜ የእስራኤል ንጉሥ ዮአስ ሊጠይቀው ሄዶ፥ ድምፁን ከፍ በማድረግ “አባቴ ሆይ! አባቴ ሆይ! አንተ እኮ የእስራኤል ሕዝብ ኀይላቸውና ጋሻ መከታቸው ነህ!” እያለ አለቀሰለት።


ኤልሳዕም ይህን ሁሉ እያየ “የእስራኤል ሠረገሎችና ፈረሰኞች የሆንክ አባቴ ሆይ! አባቴ ሆይ!” እያለ ወደ ኤልያስ ጮኸ፤ ከዚያም በኋላ ኤልያስን ዳግመኛ አላየውም። ኤልሳዕም ከኀዘን ብዛት የተነሣ ልብሱን ከሁለት ቀደደ፤


የእስራኤልም ንጉሥ ሶርያውያንን ባያቸው ጊዜ “ጌታዬ ሆይ! ልግደላቸውን? ልግደላቸውን?” ሲል ኤልሳዕን ጠየቀው።


ለድሀው አባት ነበርሁ፥ ለማላውቀውም ሰው ጠበቃ ነበርሁ።


መጎናጸፊያህንም አለብሰዋለሁ፥ በመታጠቅያህም አስታጥቀዋለሁ፥ ሹመትህንም በእጁ አሳልፌ እሰጠዋለሁ። በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ለይሁዳም ቤት አባት ይሆናል።


እፍኝ ገብስና ቁራሽ እንጀራ ለማግኘት ብላችሁ፥ ውሸት ለሚሰሙት ሕዝቤ እየዋሻችሁ፥ ሞት የማይገባቸውን ነፍሳት በመግደል፥ በሕይወትም መኖር የማይገባቸውን ነፍሳት በሕይወት በማትረፍ በሕዝቤ ፊት አርክሳችሁኛል።


እንዲህ አላቸው “አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፥ ምን ትሰጡኛላችሁ?” እነርሱም ሠላሳ ብር መዘኑለት።


ይህንንም የተናገረው ለድሆች አዝኖላቸው ሳይሆን ሌባ ስለ ነበረ ነው፤ የገንዘብ ከረጢትም ይዞ በውስጡ ከሚገባው ይወስድ ስለ ነበረ ነው።


ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፤ አንዳንዶች ይህን ሲመኙ ከእምነት ፈቀቅ በማለት መንገዳቸውን ስተው ሄደዋል፥ በብዙም ሥቃይ ራሳቸውን ወግተዋል።


ኀላፊነት የተሰጣችሁን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ ይህም በግድ ሳይሆን እንደ እግዚአብሔር ፍላጎት በፈቃደኝነት፥ ለጥቅም በመስገብገብ ሳይሆን በጽኑ ፍላጎት ይሁን፤


ስለዚህ ሌዋዊው አብሮት ለመኖር ተስማማ፤ ወጣቱም ለሚካ ከልጆቹ እንደ አንዱ ሆነለት።


ሚካም፥ “የየት አገር ሰው ነህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፥ “እኔ በይሁዳ ምድር ከምትገኝ ከቤተልሔም የመጣሁ ሌዋዊ ነኝ፤ መኖሪያ ስፍራ እፈልጋለሁ” አለው።


እርሱም፥ “ሚካ ይህን ይህን አደረገልኝ፥ ቀጠረኝ፤ ካህኑም ሆንሁ” አላቸው።


ከቤትህም የቀረው ሁሉ ይመጣል፤ በፊቱም ሰግዶ፦ ቁራሽ እንጀራ እንድበላ ከካህናት ስፍራ ወደ አንዲቱ፥ እባክህ፥ ስደደኝ ብሎ የዕለት ምግብ ብቻ ለማግኘት ይለምናል።’”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos