Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 16:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ሕዝቡም ሳምሶንን ባዩት ጊዜ፥ አምላካቸውን ዳጎንን በማመስገን፥ “ምድራችንን ያጠፋውን፥ ብዙ ሰው የገደለብንን፥ ጠላታችንን አምላካችን በእጃችን አሳልፎ ሰጠን” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ሕዝቡም ሳምሶንን ባዩት ጊዜ፣ አምላካቸውን ዳጎንን በማመስገን፣ “ምድራችንን ያጠፋውን፣ ብዙ ሰው የገደለብንን፣ ጠላታችንን፣ አምላካችን በእጃችን አሳልፎ ሰጠን” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እርሱንም ባዩት ጊዜ “ምድራችንን ያጠፋውን፥ ከእኛም ብዙ ሰው የገደለውን ጠላታችንን አምላካችን ለእኛ አሳልፎ ሰጠን” እያሉ አምላካቸውን አመሰገኑ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ሕዝ​ቡም ሁሉ ባዩት ጊዜ፥ “ምድ​ራ​ች​ንን ያጠ​ፋ​ውን፥ ከእ​ኛም ብዙ ሰው የገ​ደ​ለ​ውን ጠላ​ታ​ች​ንን አም​ላ​ካ​ችን በእ​ጃ​ችን አሳ​ልፎ ሰጠን እያሉ አም​ላ​ካ​ቸ​ውን አመ​ሰ​ገኑ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ሕዝቡም ሁሉ ባዩት ጊዜ፦ ምድራችንን ያጠፋውን፥ ከእኛም ብዙ ሰው የገደለውን ጠላታችንን አምላካችን በእጃችን አሳልፎ ሰጠን እያሉ አምላካቸውን አመሰገኑ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 16:24
14 Referencias Cruzadas  

እነዚህም ሁለት ነቢያት በምድር የሚኖሩትን ስላሠቃዩ በምድር የሚኖሩት በእነርሱ ዕጣ ደስ ይላቸዋል፤ በደስታም ይኖራሉ፤ እርስ በርሳቸውም ስጦታ ይሰጣጣሉ።


ስለዚህ ለመረቡ ይሠዋል፥ ለአሽክላውም ያጥናል። በእነርሱ ድርሻው ሰብቷልና፥ መብሉም በዝቶአልና።


ነገር ግን በፊታቸው ባወጣኋቸው በአሕዛብ ፊት ስሜ እንዳይረክስ ብዬ ስለ ስሜ ሠራሁ።


እንግዲህም አምላካችን ጌታ ሆይ፥ የምድር መንግሥታት ሁሉ አንተ ብቻ ጌታ እንደሆንህ እንዲያውቁ ከእጁ አድነን።”


ገፈፉትም፥ ራሱንና መሣሪያውንም አንሥተው ለጣዖቶቻቸውና ለሕዝቡ የምሥራች እንዲናገሩ ወደ ፍልስጥኤማውያን አገር ዙሪያ መልእክተኞችን ላኩ።


ከዚያም የሳኦልን ራስ ቆርጠው፥ የጦር መሣሪያውንም ገፈው፥ የምሥራቹን በየቤተ ጣዖቶቻቸውና በሕዝባቸው መካከል እንዲናገሩ ወደ ፍልስጥኤም ምድር ሁሉ መልክተኞች ላኩ።


ሳምሶንም፥ “በአንድ የአህያ መንጋጋ፥ ሺህ ሰው ዘራሪ፤ በአንድ የአህያ መንጋጋ፥ ሺህ ሬሳ አነባባሪ!” ብሎ ፎከረ።


ክፉኛ መታቸው፤ ከነርሱም ብዙዎችን ገደለ፤ ከዚያም ወርዶ በኢታም ዐለት ዋሻ ተቀመጠ።


ነገር ግን ጠላቶቻቸው እንዳይታበዩ፦ ‘እጃችን ከፍ ከፍ አለች እንጂ ጌታ ይህን ሁሉ አላደረገም’ እንዳይሉ፥ ስለ ጠላት ትንኮሳ አሰብኩ።”


እጅግ ደስ ባላቸው ጊዜ፥ “እንዲያዝናናን ሳምሶንን አምጡት” አሉ፤ ስለዚህ ሳምሶንን ከእስር ቤት ጠርተው አስመጡት፤ በፊታቸውም ተጫወተ። በምሶሶዎቹ መካከል ባቆሙት ጊዜ፥


ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ፥ አማልክት በሙሉ፥ ስገዱለት።


ሳምሶን ሌሒ እንደደረሰም ፍልስጥኤማውያን እየጮኹ ወደ እርሱ መጡ፤ በዚህ ጊዜ የጌታ መንፈስ በሳምሶን ላይ በኃይል ወረደበት። እጆቹ የታሰሩበትም ገመድ እሳት ውስጥ እንደ ገባ የተልባ እግር ፈትል ሆኖ ከእጆቹ ላይ ወደቀ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios