Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 15:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ከዚያም በቅርቡ የሞተ የአንድ የአህያ መንጋጋ አይቶ ከመሬት አነሣ፤ በዚያም አንድ ሺህ ሰው ገደለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ከዚያም በቅርቡ የሞተ የአንድ የአህያ መንጋጋ አይቶ ከመሬት አነሣ፤ በዚያም አንድ ሺሕ ሰው ገደለ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከዚህ በኋላ በቅርብ ጊዜ የሞተ የአንድ አህያ መንጋጋ አገኘ፤ ጐንበስ ብሎ አንሥቶም አንድ ሺህ ሰው ገደለበት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የወ​ደቀ የአ​ህያ መን​ጋጋ አጥ​ን​ት​ንም በመ​ን​ገድ አገኘ። እጁ​ንም ዘር​ግቶ ወሰ​ደው፤ በእ​ር​ሱም አንድ ሺህ ሰው ገደለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 አዲስም የአህያ መንጋጋ አገኘ፥ እጁንም ዘርግቶ ወሰደው፥ በእርሱም አንድ ሺህ ሰው ገደለ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 15:15
14 Referencias Cruzadas  

ጌታ አምላካችሁ እንደ ተናገራችሁ ስለ እናንተ የሚዋጋ እርሱ ነውና ከእናንተ አንዱ ሰው ሺህ ሰውን ያሳድዳል።


ከእናንተም አምስቱ መቶውን ያሳድዳሉ፥ መቶውም ዓሥሩን ሺህ ያሳድዳሉ፤ ጠላቶቻችሁም በእናንተ ፊት በሰይፍ ይወድቃሉ።


ከኤሁድ በኋላ ስድስት መቶ ፍልስጥኤማውያንን በበሬ መንጃ የገደለው የዓናት ልጅ ሻምጋር ተነሣ፤ እርሱም እንደዚሁ ደግሞ እስራኤልን አዳነ።


ዮናታንና ጋሻ ጃግሬው በመጀመሪያው ቀን ባደረጉት ግዳያቸው በአንድ ጥማድ የእርሻ ቦታ ላይ ሃያ ያህል ሰዎች ገደሉ።


ዮናታን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና፤ ወደነዚያ ያልተገረዙ ሰዎች ጦር ሰፈር እንሻገር፤ ምናልባትም ጌታ ይዋጋልን ይሆናል፤ በብዙም ሆነ በጥቂት ለማዳን ጌታን የሚያግደው የለምና” አለው።


ሦስቱን መቶ ሰዎች በሦስት ቡድን ከፍሎ፥ እያንዳንዱን ሰው ቀንደ መለከትና በውስጡ ችቦ ያለበት ባዶ ማሰሮ በእጁ እንዲይዝ አደረገ።


የሔቤር ሚስት ያዔል ግን ሲሣራ ደክሞ፥ ከባድ እንቅልፍም ወስዶት ሳለ፥ የድንኳን ካስማና መዶሻ ይዛ በቀስታ ወደ እርሱ ቀረበች፤ ከዚያም ካስማውን በመዶሻ ጆሮ ግንዱ ላይ መትታ ከመሬት ጋር ሰፋችው፤ እርሱም ሞተ።


የእሳትን ኃይል አጠፉ፤ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፤ ከድካማቸው ብርቱ ሆኑ፤ በጦርነት ኀይለኞች ሆኑ፤ የባዕድ ወራሪዎችን አባረሩ።


ሳምሶንም፥ “በአንድ የአህያ መንጋጋ፥ ሺህ ሰው ዘራሪ፤ በአንድ የአህያ መንጋጋ፥ ሺህ ሬሳ አነባባሪ!” ብሎ ፎከረ።


ይህን ተናግሮ እንዳበቃ የአህያውን መንጋጋ ከእጁ ወዲያ ወረወረው፤ የዚያም ቦታ ስም ራማት ሌሒሰ ተብሎ ተጠራ።


ጠላቶቻችሁንም ታሳድዳላችሁ፥ በእናንተም ፊት በሰይፍ ይወድቃሉ።


የዳዊት ኀያላን ሰዎች ስም የሚከተለው ነው፤ የታሕክሞን ሰው ዮሼብ ባሼቤት የሦስቱ አለቆች አለቃ ሲሆን፥ እርሱም ጦሩን ሰብቆ በአንድ ውጊያ ላይ ስምንት መቶ ሰው በአንዴ የገደለ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios